ኢያሱ 15:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 እርሷም፣ “እባክህ፤ ባርከኝ፤ በኔጌብ መሬት እንደ ሰጠኸኝ ሁሉ፣ አሁንም የውሃ ምንጭ ጕድጓዶች ስጠኝ” አለችው፤ ካሌብም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጮች ሰጣት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 እርሷም እንዲህ አለችው፦ “በረከትን ስጠኝ፤ በደቡብም በኩል ያለውን ምድር ሰጥተኸኛልና አሁን ደግሞ የውኃውን ምንጭ ስጠኝ።” እርሱም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 እርስዋም “የሰጠኸኝ ምድር ደረቅ ስለ ሆነ ጥቂት የውሃ ጒድጓዶች እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ” አለችው። ካሌብም ከላይና ከታች በኩል ያሉትን ሁለቱን የውሃ ምንጮች ሰጣት። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 እርስዋም፥ “በረከትን ስጠኝ፤ በደቡብ በኩል ያለውን ምድር ሰጥተኸኛልና አሁን ደግሞ የውኃውን ምንጭ ስጠኝ” አለችው። እርሱም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ካሌብም፦ ምን ፈለግሽ? አላት። እርስዋም፦ በረከትን ስጠኝ፥ በደቡብም በኩል ያለውን ምድር ሰጥተኸኛልና አሁን ደግሞ የውኃውን ምንጭ ስጠኝ አለችው። እርሱም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት። 参见章节 |