Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 13:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ማለት በደጋው አገር የሚገኙት ከተሞች ሁሉና መቀመጫውን በሐሴቦን አድርጎ የገዛውን የአሞራውያንን ንጉሥ የሴዎንን ግዛት በሙሉ ያካትታል። ሙሴ ሴዎንንና በዚያው ምድር ተቀማጭ የነበሩትን መሳፍንት፤ ኤዊ፣ ሮቆም፣ ሱር፣ ሑርና ሪባ የተባሉትን የምድያም አለቆች ድል አደረጋቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የሜዳውም ከተሞች ሁሉ፥ በሐሴቦንም የነገሠው የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ሁሉ ነበረ፤ ሙሴም ሴዎንና በምድሪቱ የተቀመጡትን የሴዎንን መሳፍንት፥ የምድያምን አለቆች ኤዊን፥ ሮቆምን፥ ሱርን፥ ሑርን፥ ሪባን ድል ነሣቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በደጋማው አገር የሚገኙትን ከተሞችና መኖሪያውን በሐሴቦን አድርጎ ይገዛ የነበረውን የአሞራውያን ንጉሥ የሲሖንን ግዛት ሁሉ ይጨምራል። ሙሴም ንጉሥ ሲሖንንና የምድያም መሪዎች የነበሩትን፥ ኤዊን፥ ሬቄምን፥ ጹርን፥ ሑርንና ሬባዕን ድል ነሣ፤ እነዚህ ሁሉ ምድሪቱን የሚያስተዳድሩት የንጉሥ ሲሖን ገባሮች በመሆን ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የሚ​ሶር ከተ​ሞች ሁሉ፥ በሐ​ሴ​ቦ​ንም የነ​ገ​ሠው የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ንጉሥ የሴ​ዎን መን​ግ​ሥት ሁሉ ነበረ፤ ሙሴም እር​ሱ​ንና በም​ድ​ሪቱ የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን የሴ​ዎ​ንን መሳ​ፍ​ንት፥ የም​ድ​ያ​ምን አለ​ቆች ኤዊን፥ ሮቦ​ቅን፥ ሱርን፥ ኡርን፥ ሮቤን በሲ​ዮን የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ገደ​ላ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የሜዳውም ከተሞች ሁሉ፥ በሐሴቦንም የነገሠው የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ሁሉ ነበረ፥ ሙሴም እርሱንና በምድሪቱ የተቀመጡትን የሴዎንን መሳፍንት፥ የምድያምን አለቆች ኤዊን፥ ሮቆምን፥ ሱርን፥ ሑርን፥ ሪባን መታቸው።

参见章节 复制




ኢያሱ 13:21
6 交叉引用  

እንዲሁም የተገደለችዋ ምድያማዊት ሴት ከስቢ ትባላለች፤ እርሷም ከምድያማውያን ቤተ ሰብ የአንዱ ነገድ አለቃ የሆነው የሱር ልጅ ነበረች።


ከተገደሉትም መካከል ዐምስቱ የምድያም ነገሥታት ኤዊ፣ ሮቆም፣ ሱር፣ ሑርና ሪባ ይገኙባቸዋል፤ የቢዖርን ልጅ በለዓምንም በሰይፍ ገደሉት።


በከፍታው ቦታ ላይ የሚገኙትን ከተሞች በሙሉ፣ ገለዓድን እንዳለ፣ እስከ ሰልካና እስከ ኤድራይ ያለውን ባሳንን ሁሉ እንዲሁም በባሳን ውስጥ የሚገኙትን የዐግ ግዛት ከተሞች በእጃችን አደረግን።


ቤተ ፌጎርን፣ የፈስጋን ሸንተረሮችና ቤትየሺሞትን፣


跟着我们:

广告


广告