Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮናስ 1:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከዚያም መርከበኞቹ እርስ በርሳቸው፣ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንደ መጣብን ለማወቅ፣ ኑ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እርስ በእርሳቸውም፦ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንደመጣብን እንድናውቅ ኑ፥ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፥ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 በመርከቢቱ ውስጥ የነበሩትም ሁሉ እርስ በርሳቸው “በዚህ አደጋ ላይ እንድንወድቅ ምክንያት የሆነው ማን እንደ ሆነ ለማወቅ ኑ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወጣ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክ​ን​ያት እንደ አገ​ኘን እና​ውቅ ዘንድ ኑ፤ ዕጣ እን​ጣ​ጣል” ተባ​ባሉ። ዕጣም ተጣ​ጣሉ፤ ዕጣ​ውም በዮ​ናስ ላይ ወደቀ።

参见章节 复制




ዮናስ 1:7
18 交叉引用  

ንጉሥ ጠረክሲስ በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት ኒሳን በተባለው በመጀመሪያው ወር፣ ቀኑንና ወሩን ለመለየት ፉር የተባለ ዕጣ ሐማ ባለበት ጣሉ፤ ዕጣውም አዳር በተባለው በዐሥራ ሁለተኛው ወር ላይ ወደቀ።


እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፤ በምን ላይ እንዳልተስማማን ንገረኝ እንጂ አትፍረድብኝ።


ልብሶቼን ተከፋፈሉ፤ በእጀ ጠባቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።


ዕጣ በጕያ ውስጥ ይጣላል፤ ውሳኔው በሙሉ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።


“ይህን ባታደርጉ ግን እግዚአብሔርን ትበድላላችሁ፤ ኀጢአታችሁ እንደሚያገኛችሁም ዕወቁ።


ከሰቀሉትም በኋላ ዕጣ ጥለው ልብሱን ተካፈሉ፤


በከነዓን ምድር የነበሩትንም ሰባት መንግሥታት አጥፍቶ፣ ምድራቸውን ለገዛ ሕዝቡ ርስት አድርጎ አወረሳቸው።


ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ በምንም ነገር አትፍረዱ፤ ጌታ እስኪመጣ ጠብቁ። እርሱ በጨለማ ውስጥ የተሰወረውን ወደ ብርሃን ያመጣዋል፤ በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውንም ሐሳብ ይገልጠዋል። በዚያ ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የሚገባውን ምስጋና ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።


እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “ተነሥ! ለምን በግንባርህ ተደፋህ?


跟着我们:

广告


广告