Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮናስ 1:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እርሱም፣ “ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንደ መጣባችሁ ዐውቃለሁ፤ አንሥታችሁ ወደ ባሕሩ ጣሉኝ፤ ባሕሩም ጸጥ ይላል” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እርሱም፦ “ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንደመጣባችሁ አውቃለሁና አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፥ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ዮናስም “ይህ ማዕበል በእናንተ ላይ የመጣው በእኔ በደል ምክንያት እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፤ ስለዚህ እኔን አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፤ ማዕበሉም ጸጥ ይልላችኋል” አላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እር​ሱም፥ “ይህ ታላቅ ማዕ​በል በእኔ ምክ​ን​ያት እንደ አገ​ኛ​ችሁ ዐው​ቃ​ለ​ሁና አን​ሥ​ታ​ችሁ ወደ ባሕሩ ጣሉኝ፤ ባሕ​ሩም ጽጥ ይል​ላ​ች​ኋል” አላ​ቸው።

参见章节 复制




ዮናስ 1:12
10 交叉引用  

ዳዊት ሕዝቡን የሚቀሥፈውን መልአክ ባየ ጊዜ እግዚአብሔርን፣ “እነሆ ኀጢአት የሠራሁትም የተሳሳትሁም እኔ ነኝ፤ እነዚህ ግን በጎች ናቸው፤ ምን አጠፉ? እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን” አለ።


ዳዊት እግዚአብሔርን፣ “ተዋጊዎቹ እንዲቈጠሩ ያዘዝሁ እኔ አይደለሁምን? ኀጢአት የሠራሁትም ሆነ የተሳሳትሁም እኔ ነኝ፤ እነዚህ እኮ በጎች ናቸው፤ ታዲያ እነርሱ ምን አደረጉ? እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን እንጂ፣ መቅሠፍቱ በሕዝብህ ላይ አይውረድ” አለ።


ክፋትህ የሚጐዳው እንደ አንተ ያለውን ሰው ብቻ ነው፤ ጽድቅህም የሚጠቅመው የሰውን ልጆች ብቻ ነው።


ጥበብ ከጦር መሣሪያ ይበልጣል፤ ነገር ግን አንድ ኀጢአተኛ ብዙ መልካም ነገርን ያጠፋል።


የባሕሩም ማዕበል እጅግ እየበረታ ስለ ሄደ፣ “ባሕሩ ጸጥ እንዲልልን በአንተ ላይ ምን ብናደርግ ይሻላል?” አሉት።


ሰዎቹ ግን ባላቸው ኀይል እየቀዘፉ ወደ የብስ ለመጠጋት ሞከሩ፤ ይሁን እንጂ አልቻሉም፤ ባሕሩ የባሰ ይናወጥ ነበርና።


ሕዝቡ ሁሉ ከሚጠፋ ስለ ሕዝቡ አንድ ሰው ቢሞት የሚሻል መሆኑን አታስተውሉም።”


‘ጳውሎስ ሆይ፤ አትፍራ፤ በቄሳር ፊት መቆም ይገባሃል፤ ከአንተ ጋራ የሚጓዙትንም ሰዎች ሕይወት እግዚአብሔር አትርፎልሃል’ አለኝ።


እንግዲህ እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን ለመቋቋም ያልቻሉት በዚህ ምክንያት ነው። ጀርባቸውን አዙረው የሸሹትም ለጥፋት በመዳረጋቸው ነው። ዕርም የሆነውን ነገር ከመካከላችሁ ካላጠፋችሁ፣ ከዚህ በኋላ ከእናንተ ጋራ አልሆንም።


跟着我们:

广告


广告