Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 19:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ስለዚህ፣ “ዕጣ ተጣጥለን ለሚደርሰው ይድረስ እንጂ አንቅደደው” ተባባሉ። ይህም የሆነው፣ “ልብሴን ተከፋፈሉት፤ በእጀ ጠባቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ” የሚለው የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው። ወታደሮቹ ያደረጉትም ይህንኑ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ስለዚህም እርስ በርሳቸው “ለማን እንዲሆን ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው” ተባባሉ። ይህም “ልብሴን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ፤ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉበት” የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነበር። ወታደሮቹም እንዲህ አደረጉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ስለዚህ ወታደሮቹ “ለማን እንደሚደርስ ለማወቅ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ፥ አንቅደደው” ተባባሉ። ይህም የሆነው፥ “ልብሴን ተከፋፈሉ፤ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉ” የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ወታደሮቹም እንዲሁ አደረጉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ዕጣ እን​ጣ​ጣ​ልና ለደ​ረሰ ይድ​ረ​ሰው እንጂ አን​ቅ​ደ​ደው ተባ​ባሉ፤” ይህም “ልብ​ሶ​ችን ለራ​ሳ​ቸው ተካ​ፈሉ፤ በቀ​ሚ​ሴም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣሉ” ያለው የመ​ጽ​ሐፍ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው፤ ጭፍ​ሮ​ችም እን​ዲሁ አደ​ረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው፦ “ለማን እንዲሆን በእርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው” ተባባሉ። ይህም፦ “ልብሴን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉበት” የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።

参见章节 复制




ዮሐንስ 19:24
13 交叉引用  

በዚህም እግዚአብሔር ለኢዩ፣ “ልጆችህ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ዙፋን ላይ ይቀመጣሉ” ሲል የተናገረው ቃል ተፈጸመ።


ልብሶቼን ተከፋፈሉ፤ በእጀ ጠባቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።


ከላይ በኩል በመካከሉ ዐንገትጌ አድርገህ አብጀው፤ እንዳይቀደድም በማስገቢያው ዙሪያ እንደ ክሳድ ያለ ዝምዝም ጠርዝ ሥራለት።


እርሱ ግን እንዲህ አላሰበም፤ በልቡም ይህ አልነበረም፤ ነገር ግን ዕቅዱ ለማጥፋት፣ ብዙ ሕዝቦችንም ለመደምሰስ ነበር።


ከሰቀሉትም በኋላ ዕጣ ጥለው ልብሱን ተካፈሉ፤


ከዚያም ሰቀሉት፤ እያንዳንዱም ምን እንደሚደርሰው ለማወቅ ዕጣ ተጣጥለው ልብሱን ተከፋፈሉ።


ኢየሱስም፣ “አባት ሆይ፤ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” አለ። እነርሱም ልብሱን በዕጣ ተከፋፈሉት።


የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን ‘አማልክት’ ካላቸውና መጽሐፍም ሊሻር የማይቻል ከሆነ፣


“ስለ ሁላችሁ መናገሬ አይደለም፤ የመረጥኋቸውን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን፣ ‘እንጀራዬን የሚበላ ተረከዙን አነሣብኝ’ የሚለው የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው።


ከዚያም ኢየሱስ ሁሉ ነገር እንደ ተፈጸመ ዐውቆ፣ የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም፣ “ተጠማሁ” አለ።


የኢየሩሳሌም ሰዎችና አለቆቻቸው ኢየሱስን አላወቁትም፤ ይሁን እንጂ በየሰንበቱ የሚነበበው የነቢያት ቃል እንዲፈጸም በርሱ ፈረዱበት።


跟着我们:

广告


广告