Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 18:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት ሲሞቅ፣ “አንተ ከርሱ ደቀ መዛሙርት አንዱ አይደለህምን?” አሉት። እርሱም፣ “እኔ አይደለሁም” ሲል ካደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር። “አንተስ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ አይደለህምን?” አሉት። እርሱም “አይደለሁም፤” ብሎ ካደ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 የዚያን ጊዜ ስምዖን ጴጥሮስ ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር፤ ሌሎች ሰዎችም “አንተስ ከኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አንዱ አይደለህምን?” አሉት። እርሱም “አይደለሁም” ብሎ ካደ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር፤ “አን​ተስ ከእ​ርሱ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ወገን አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?” አሉት፤ እር​ሱም፥ “አይ​ደ​ለ​ሁም” ብሎ ካደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር። እንግዲህ፦ “አንተ ደግሞ ከደቀ መዛሙርቱ አይደለህምን?” አሉት። እርሱም፦ “አይደለሁም” ብሎ ካደ።

参见章节 复制




ዮሐንስ 18:25
13 交叉引用  

ሣራ ስለ ፈራች፣ “ኧረ አልሣቅሁም” ብላ ዋሸች። እርሱ ግን፣ “ሣቅሽ እንጂ” አላት።


ሰውን መፍራት ወጥመድ ነው፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን በሰላም ይኖራል።


ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ ተቀምጦ ሳለ አንዲት የቤት ሠራተኛ ወደ እርሱ ቀርባ፣ “አንተም ከገሊላው ኢየሱስ ጋራ ነበርህ” አለችው።


ጴጥሮስ በግቢው ውስጥ በታችኛው በኩል ሳለ፣ ከሊቀ ካህናቱ የቤት ሠራተኞች አንዲቱ መጣች፤


ሰዎቹ በሊቀ ካህናቱ ግቢ ውስጥ እሳት አንድደው በአንድነት ተቀምጠው ሳለ፣ ጴጥሮስም ከእነርሱ ጋራ ተቀምጦ ነበር።


አንዲት የቤት ሠራተኛም ጴጥሮስ እሳቱ አጠገብ ተቀምጦ አየችውና ትኵር ብላ በመመልከት፣ “ይህ ሰው ደግሞ ከርሱ ጋራ ነበረ” አለች።


እርሱ ግን፣ “አንቺ ሴት፤ እኔ ዐላውቀውም” ብሎ ካደ።


跟着我们:

广告


广告