ዮሐንስ 13:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ኢየሱስም፣ “ገላውን የታጠበ ሰው የሚያስፈልገው እግሩን ብቻ መታጠብ ነው፤ የቀረው አካሉ ግን ንጹሕ ነው። ሁላችሁም ባትሆኑ፣ እናንተ ንጹሓን ናችሁ” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ኢየሱስም “ሰውነቱን የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፤ ሁለንተናው ግን ንጹሕ ነው፤ እናንተም ንጹሐን ናችሁ፤ ነገር ግን ሁላችሁም አይደላችሁም፤” አለው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ኢየሱስም “ሰውነቱን የታጠበ ሁለመናውም ንጹሕ በመሆኑ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፤ እናንተም ንጹሖች ናችሁ፤ ነገር ግን ሁላችሁም ንጹሖች አይደላችሁም” አለው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ጌታችን ኢየሱስም፥ “ፈጽሞ የታጠበ ከእግሩ በቀር ሊታጠብ አያስፈልገውም፤ ሁለንተናው ንጹሕ ነውና፤ እናንተማ ንጹሓን ናችሁ፤ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ኢየሱስም፦ “የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፥ ሁለንተናው ግን ንጽሕ ነው፤ እናንተም ንጹሐን ናችሁ፥ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም” አለው። 参见章节 |