Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 9:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ንጹሕ ብሆን እንኳ፣ አንደበቴ ይፈርድብኛል፤ እንከን የለሽ እንኳ ብሆን፣ በደለኛ ያደርገኛል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ጻድቅ ብሆን እንኳን አፌ ይወቅሰኛል፥ ፍጹምም ብሆን ጠማማ ያደርገኛል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እኔ ንጹሕና እውነተኛ ነኝ፤ ነገር ግን አነጋገሬ በደለኛ ያደርገኛል፤ የምናገራቸው ንግግሮች ሁሉ ይፈርዱብኛል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ጻድቅ ብሆን አፌ ይወ​ቅ​ሰ​ኛል፤ ፍጹ​ምም ብሆን ጠማማ ያደ​ር​ገ​ኛል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ጻድቅ ብሆን አፌ ይወቅሰኛል፥ ፍጹምም ብሆን ጠማማ ያደርገኛል።

参见章节 复制




ኢዮብ 9:20
24 交叉引用  

ዖፅ በሚባል አገር የሚኖር ኢዮብ የተባለ ሰው ነበረ፤ ይህ ሰው ነቀፋ የሌለበት፣ ቅን፣ እግዚአብሔርን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ነበር።


በደለኛ ብሆን ወዮልኝ፤ ንጹሕ ብሆንም፣ ራሴን ቀና አላደርግም፤ ውርደትን ተከናንቤአለሁና፤ በመከራም ተዘፍቄአለሁ።


መተላለፌ በከረጢት ይቋጠራል፤ ኀጢአቴንም ትሸፍናለህ።


‘ኢዮብ ያለ ዕውቀት ይናገራል፤ ቃሉም ማስተዋል ይጐድለዋል።’


ስለዚህ ኢዮብ አፉን በከንቱ ይከፍታል፤ ዕውቀት አልባ ቃላትም ያበዛል።”


‘ሥጋ ለባሽ ከእግዚአብሔር ይልቅ ጻድቅ ሊሆን ይችላልን? ሰውስ ከፈጣሪው ይልቅ ንጹሕ ሊሆን ይችላልን?


ጻድቅ ብሆንም እንኳ፣ ልመልስለት አልችልም፤ ዳኛዬን ምሕረት ከመለመን ሌላ ላደርግ የምችለው የለም።


“በርግጥ ነገሩ እንዲህ እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ሥጋ ለባሽ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ጻድቅ ሊሆን ይችላል?


ንጹሕ አድርገህ እንደማትቈጥረኝ ስለማውቅ፣ መከራዬን ሁሉ እፈራለሁ።


በደለኛ መሆኔ ካልቀረ፣ ለምን በከንቱ እለፋለሁ?


እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአትን ብትቈጣጠር፣ ጌታ ሆይ፤ ማን ሊቆም ይችላል?


ሰው ሆኖ በፊትህ ጻድቅ የለምና፣ ባሪያህን ወደ ፍርድ አታቅርበው።


ከቃላት ብዛት ኀጢአት አይታጣም፤ አንደበቱን የሚገታ ግን ጠቢብ ነው።


ጠማማ ልብ ያለው ሰው አይሳካለትም፤ በአንደበቱ የሚቀላምድም መከራ ላይ ይወድቃል።


እኔም፣ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይተዋልና ጠፍቻለሁ፣ ወዮልኝ!” አልሁ።


ሰውየውም ራሱን ጻድቅ ለማድረግ ፈልጎ፣ “ለመሆኑ ባልንጀራዬ ማን ነው?” አለው።


እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ በሰዎች ፊት ራሳችሁን የምታጸድቁ ናችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ልባችሁን ያውቃል፤ በሰዎች ዘንድ የከበረ፣ በእግዚአብሔር ፊት የረከሰ ነውና።


እውነትን በተቀሙና መንፈሳዊው ነገር ትርፍ ማግኛ በሚመስላቸው፣ አእምሮ በጐደላቸው ሰዎችም መካከል የማያባራ ንትርክ ያመጣሉ።


ሁላችንም በብዙ ነገር እንሰናከላለን፤ በንግግሩ የማይሰናከል ማንም ሰው ቢኖር፣ እርሱ ሰውነቱን ሁሉ መቈጣጠር የሚችል ፍጹም ሰው ነው።


跟着我们:

广告


广告