Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 7:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 አካሌ ቈስሎ ትልና ቅርፊት ለብሷል፤ ቈዳዬ አፈክፍኳል፤ ቍስሌም አመርቅዟል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሥጋዬ ትልና ጓል ለብሶአል፥ ቆዳዬ ያፈከፍካል እንደገናም ይመግላል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 መላ ሰውነቴ በትል ተሞልቶአል፤ ሥጋዬም በቅርፊት ተሸፍኖአል፤ ፈንድቶም ይመግላል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሥጋዬ በት​ልና በመ​ግል በስ​ብ​ሶ​አል፥ ቍስ​ሌን በገል እያ​ከ​ክሁ አለ​ቅሁ። ዐመ​ድም ሆንሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሥጋዬ ትልና ጓል ለብሶአል፥ ቁርበቴ ያፈከፍካል እንደ ገናም ይመግላል።

参见章节 复制




ኢዮብ 7:5
15 交叉引用  

“እንደ በሰበሰ ግንድ፣ ብል እንደ በላው ልብስ፣ ሕይወት እያደር ማለቅ ነው።


መበስበስን፣ ‘አንተ አባቴ ነህ፤’ ትልንም፣ ‘አንቺ እናቴ’ ወይም ‘እኅቴ ነሽ’ ካልሁ፣


ዐይኔ ከሐዘን የተነሣ ፈዘዘ፤ መላ አካሌም እንደ ጥላ ሆነ።


ቈዳና ዐጥንት ብቻ ሆኜ ቀረሁ፤ ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።


ቈዳዬ ቢጠፋም፣ ከሥጋዬ ብለይም፣ እግዚአብሔርን አየዋለሁ፤


የተሸከመቻቸው ማሕፀን ትረሳቸዋለች፤ ትል ይቦጠቡጣቸዋል፤ ክፉዎች እንደ ዛፍ ይሰበራሉ፤ የሚያስታውሳቸውም የለም።


ልብሴ እንኳ እስኪጸየፈኝ ድረስ፣ በዐዘቅት ውስጥ ታሰጥመኛለህ።


ከእግር ጥፍራችሁ እስከ ራስ ጠጕራችሁ ጤና የላችሁም፤ ቍስልና ዕባጭ እንዲሁም እዥ ብቻ ነው፤ አልታጠበም፤ አልታሰረም፤ በዘይትም አልለዘበም።


ክብርህ፣ ከነበገና ድምፁ ወደ ሲኦል ወረደ፤ ብሎች ከበታችህ ተነጥፈዋል፤ ትሎችም መደረቢያህ ይሆናሉ።


“ወጥተውም በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤ የሚበሏቸው ትሎች አይሞቱም፤ የሚያቃጥላቸው እሳታቸው አይጠፋም፤ ለሰውም ዘር ሁሉ አስጸያፊ ይሆናሉ።”


በዚያም መንገዳችሁንና ራሳችሁን ያረከሳችሁበትን ተግባር ሁሉ ታስታውሳላችሁ፤ በፈጸማችሁትም ክፋት ሁሉ ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።


ሄሮድስም ለእግዚአብሔር ክብር ስላልሰጠ የጌታ መልአክ ወዲያው መታው፤ በትልም ተበልቶ ሞተ።


跟着我们:

广告


广告