Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 6:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 የተናገርሁትን ለማረም፣ ተስፋ የቈረጠውንም ሰው ቃል እንደ ነፋስ ለመቍጠር ታስባላችሁን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ተስፋ የሌለው ሰው ንግግር እንደ ነፋስ ነውና ቃሌን ትገሥጹ ዘንድ ታስባላችሁን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እናንተ የእኔን ንግግር እንደ ነፋስ ባዶ አድርጋችሁ ትቈጥሩታላችሁ፤ ታዲያ፥ ተስፋ ለቈረጥሁት ለእኔ መልስ መስጠት ለምን ትፈልጋላችሁ?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 የን​ግ​ግ​ራ​ች​ሁም ማጽ​ና​ናት ዕረ​ፍ​ትን አይ​ሰ​ጠ​ኝም፤ የአ​ን​ደ​በ​ታ​ች​ሁም ቅል​ጥ​ፍና ደስ አያ​ሰ​ኘ​ኝም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ተስፋ የሌለው ሰው ንግግር እንደ ነፋስ ነውና ቃሌን ትገሥጹ ዘንድ ታስባላችሁን?

参见章节 复制




ኢዮብ 6:26
19 交叉引用  

“ሕይወቴን እጅግ ጠላሁ፤ ስለዚህም ማጕረምረሜን ያለ ገደብ እለቅቃለሁ፤ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ።


“ጠቢብ ሰው በከንቱ ንግግር መልስ ይሰጣልን? ወይስ በምሥራቅ ነፋስ ሆዱን ይሞላል?


ይህ ከንቱ ንግግር አያልቅምን? ትለፈልፍ ዘንድ የሚገፋፋህ ምንድን ነው?


እርሱም፣ “አነጋገርሽ እንደ ሞኝ ሴት ነው፤ መልካሙን ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀበልን፤ ክፉውንስ አንቀበልምን? አላት።” በዚህ ሁሉ፣ ኢዮብ በንግግሩ አልበደለም።


“ዕውቀት በጐደለው ቃል፣ ዕቅዴን የሚያጨልም ይህ ማን ነው?


አንድ ጊዜ ተናገርሁ፤ የምመልሰው የለኝም፤ ሁለተኛም ተናገርሁ፤ ከእንግዲህ አንዳች አልጨምርም።”


“ፍርዴን ታቃልላለህን? ወይስ አንተ ጻድቅ ለመሆን እኔን ትኰንናለህ?


አንተ፣ ‘ያለ ዕውቀት ዕቅዴን የሚያደበዝዝ ይህ ማን ነው?’ አልኸኝ፤ በርግጥ ያልገባኝን ነገር፣ የማላውቀውንና ላስተውለው የማልችለውን ጕዳይ ተናገርሁ።


እግዚአብሔር ይህን ለኢዮብ ከተናገረ በኋላ፣ ቴማናዊውን ኤልፋዝን እንዲህ አለው፤ “እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ቅን ነገር ስላልተናገራችሁ፣ ቍጣዬ በአንተና በሁለቱ ባልንጀሮችህ ላይ ነድዷል።


የቅንነት ቃል ምንኛ ኀያል ነው! የእናንተ ክርክር ግን ምን ፋይዳ አለው?


ሁሉን ቻይ አምላክ ፍላጻ በውስጤ ነው፤ መንፈሴም መርዙን ትጠጣለች፤ የእግዚአብሔር ማስደንገጥ ተሰልፎብኛል።


እግዚአብሔር አድቅቆ ያጠፋኝ ዘንድ፣ ምነው እጁ በተፈታ!


“እንዲህ ያለውን ነገር የምትናገረው፣ ቃልህም እንደ ብርቱ ነፋስ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?


ኤፍሬም የነፋስ እረኛ ነው፤ ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤ ሐሰትንና ዐመፅን ያበዛል። ከአሦር ጋራ ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ የወይራ ዘይትንም ወደ ግብጽ ይልካል።


ምክንያቱም ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህ፤ ከቃልህም የተነሣ ይፈረድብሃልና።”


ከእንግዲህ በማዕበል ወደ ፊትና ወደ ኋላ እየተነዳን፣ በልዩ ልዩ ዐይነት የትምህርት ነፋስ፣ በሰዎችም ረቂቅ ተንኰልና ማታለል ወዲያና ወዲህ እየተንገዋለልን ሕፃናት አንሆንም።


跟着我们:

广告


广告