Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 6:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ወንድሞቼ ግን እንደማያዛልቅ ጅረት፣ ለጊዜው ሞልቶ እንደሚፈስስ ወንዝ የማይታመኑ ናቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ወንድሞቼ እንደ ፈፋ፥ እንደሚያልፍ ፈፋ ሐሰተኞች ሆኑብኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ወንድሞቼ ግን ጐርፉ ከወረደ በኋላ እንደሚደርቁና እንደማያስተማምኑ ወንዞች አታላዮች ናቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 “ወን​ድ​ሞ​ቼም እንደ ደረቅ ወንዝ፥ እንደ አለፈ ማዕ​በ​ልም አላ​ወ​ቁ​ኝም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ወንድሞቼ እንደ ፈፋ፥ እንደሚያልፍ ፈፋ ሐሰተኞች ሆኑብኝ።

参见章节 复制




ኢዮብ 6:15
20 交叉引用  

መከራህን ትረሳለህ፤ ዐልፎ እንደ ሄደ ጐርፍም ታስበዋለህ።


እናንተ ግን፣ በሐሰት የምትለብጡ ናችሁ፤ ሁላችሁ የማትረቡ ሐኪሞች ሆናችኋል።


ውሃ ከባሕር ውስጥ እንደሚያልቅ፣ የወንዝ ውሃም ጠፍቶ እንደሚደርቅ፣


“ወንድሞቼን ከእኔ አርቋል፤ ከሚያውቁኝም ተገለልሁ።


የቅርብ ወዳጆቼ ሁሉ ተጸየፉኝ፤ የምወድዳቸውም በላዬ ተነሡ፤


በረዶ በሟሟ ጊዜ ወንዙ ይደፈርሳል፤ ዐመዳይም በቀለጠ ጊዜ ይሞላል፤


ከቍስሌ የተነሣ ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ሸሹኝ፤ ጎረቤቶቼም ርቀው ቆሙ።


እንጀራዬን የበላ፣ የምተማመንበትም የቅርብ ወዳጄ፣ ተረከዙን አነሣብኝ።


ወዳጄንና ባልንጀራዬን ከእኔ አራቅህ፤ ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ።


በመከራ ጊዜ በወስላታ ሰው መተማመን፣ በተበላሸ ጥርስና በሰለለ እግር እንደ መታመን ነው።


ወንድሞችህና የገዛ ቤተ ሰብህ፣ እነርሱ እንኳ አሢረውብሃል፣ በአንተም ላይ ይጮኻሉ፤ በመልካም ቢናገሩህም እንኳ አትመናቸው።


ሕመሜ ለምን ጸናብኝ? ቍስሌስ ለምን በረታብኝ? ለምንስ የማይፈወስ ሆነ? እንደሚያታልል ወንዝ፣ እንደሚያሳስት ምንጭ ትሆንብኛለህን?


ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤ ስለ አንተም ግድ የላቸውም። ጠላት እንደሚመታ መታሁህ፤ እንደ ጨካኝም ቀጣሁህ፤ በደልህ ታላቅ፣ ኀጢአትህም ብዙ ነውና።


በይሁዳ ቤተ መንግሥት የቀሩ ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎናውያን ባለሥልጣኖች ይወሰዳሉ፤ ሴቶቹም እንዲህ ይላሉ፤ “ ‘እነዚያ የተማመንህባቸው ወዳጆችህ፣ አሳሳቱህ፤ አሸነፉህ። እግርህ ጭቃ ውስጥ ተሰንቅሯል፤ ወዳጆችህ ጥለውህ ሄደዋል።’


“ስለ ሁላችሁ መናገሬ አይደለም፤ የመረጥኋቸውን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን፣ ‘እንጀራዬን የሚበላ ተረከዙን አነሣብኝ’ የሚለው የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው።


እነሆ፤ ሁላችሁም በየፊናችሁ የምትበታተኑበት ጊዜ ይመጣል፤ ያም ጊዜ አሁን ነው። እኔንም ብቻዬን ትተዉኛላችሁ፤ ይሁን እንጂ አባቴ ከእኔ ጋራ ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።


እነዚህ ሰዎች በፍቅር ግብዣችሁ ላይ ያለ አንዳች ኀፍረት ከእናንተ ጋራ ቀርበው የሚበሉ ነውረኞች ናቸው፤ ደግሞም ራሳቸውን ብቻ የሚመግቡ እረኞች ናቸው፤ እነርሱም በነፋስ የሚነዱ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች ናቸው፤ በመከር ወራት ፍሬ የማይገኝባቸው ከሥራቸው ተነቅለው ሁለት ጊዜ የሞቱ ዛፎች ናቸው።


跟着我们:

广告


广告