Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 40:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “ከሁሉን ቻይ አምላክ ጋራ ተከራክሮ የሚረታው አለን? እግዚአብሔርን የሚወቅሥ እርሱ መልስ ይስጥ!”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን የሚችል አምላክን መተቸት ይችላልን? ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋቀስ እርሱ ይመልስለት።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “ኢዮብ ሆይ! ለመሆኑ ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ከእኔ ጋር ተከራክሮ ሊረታ የሚችል ይመስልሃልን? ከእኔ ከእግዚአብሔር ጋር የምትከራከር አንተ ስለ ሆንክ፥ እስቲ መልስ ስጥ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “በውኑ የሚ​ከ​ራ​ከር ሰው ሁሉን ከሚ​ችል አም​ላክ ጋር ይከ​ራ​ከ​ራ​ልን? ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር የሚ​ዋ​ቀስ እርሱ ይመ​ል​ስ​ለት።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር ይከራከራልን? ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋቀስ እርሱ ይመልስለት።

参见章节 复制




ኢዮብ 40:2
35 交叉引用  

እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፤ በምን ላይ እንዳልተስማማን ንገረኝ እንጂ አትፍረድብኝ።


ነገር ግን ከሁሉን ቻይ አምላክ ጋራ መነጋገር እፈልጋለሁ፤ ከእግዚአብሔርም ጋራ መዋቀሥ እሻለሁ።


ጕዳዬን በፊቱ አቀርብ ነበር፤ አፌንም በሙግት እሞላው ነበር።


“ፍትሕ የነሣኝ ሕያው እግዚአብሔርን! ነፍሴንም መራራ ያደረጋት፣ ሁሉን ቻይ አምላክን!


“በመከራ ላሉት ብርሃን፣ ነፍሳቸው ለተማረረች ሕይወት ለምን ተሰጠ?


መንገዱ ለተሰወረበት ሰው፤ እግዚአብሔርም በዐጥር ላጠረው፣ ሕይወት ለምን ተሰጠ?


ተመልሰህ ጨካኝ ሆንህብኝ፤ በክንድህም ብርታት አስጨነቅኸኝ።


“ምነው የሚሰማኝ ባገኝ! የመከላከያ ፊርማዬ እነሆ፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ይመልስልኝ፤ ከሳሼም ክሱን በጽሑፍ ያቅርብ።


የሰውን አቤቱታ እንደማይሰማ፣ ለምን ታማርርበታለህ?


እስኪ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤ እኔ ልጠይቅህ፣ አንተም መልስልኝ።


እግዚአብሔርም ኢዮብን እንዲህ አለው፤


ኢዮብም ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፤


በላዬ ጠባቂ ታደርግ ዘንድ፣ እኔ ባሕር ነኝን ወይስ የባሕር አውሬ?


ሰው ከርሱ ጋራ ለመከራከር ቢፈልግ፣ ከሺሕ ጥያቄ አንዱን እንኳ መመለስ አይችልም።


አሁን ያለው ሁሉ አስቀድሞ ስም የተሰጠው ነው፤ ሰው የሚሆነውም አስቀድሞ የታወቀ ነው፤ ከራሱ ይልቅ ከሚበረታ ጋራ፣ ማንም አይታገልም።


ዕውቀት ለማግኘት እግዚአብሔር ማንን አማከረ? ትክክለኛውንስ መንገድ ማን አስተማረው? ዕውቀትን ያስተማረው፣ የማስተዋልንም መንገድ ያሳየው ማን ነበር?


የሚያጸድቀኝ በአጠገቤ አለ፤ ታዲያ ማን ሊከስሰኝ ይችላል? እስኪ ፊት ለፊት እንጋጠም! ተቃዋሚዬስ ማን ነው? እስኪ ይምጣ!


ባቢሎን ሆይ፤ ወጥመድ ዘርግቼልሻለሁ፤ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፤ እግዚአብሔርን ተገዳድረሻልና፣ ተገኘሽ፤ ተያዝሽም።


“ስለ እስራኤል ምድር፣ “ ‘አባቶች ጐምዛዛ የወይን ፍሬ በሉ፤ የልጆችንም ጥርስ አጠረሰ’ እያላችሁ የምትመስሉት ተምሳሌት ምን ለማለት ነው?


ክፍያውን ሲቀበሉ በባለቤቱ ላይ በማጕረምረም፣


ጌታን እናስቀናውን? በብርታትስ ከርሱ እንበልጣለንን?


“ያስተምረው ዘንድ፣ የጌታን ልብ ያወቀ ማን ነው?” እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።


跟着我们:

广告


广告