Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 37:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የእግዚአብሔር ድምፅ በሚያስደንቅ ሁኔታ ያንጐደጕዳል፤ እኛ የማናስተውለውንም ታላቅ ነገር ያደርጋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እግዚአብሔር በአስደናቂ ሁኔታ በድምፁ ያንጐደጉዳል፥ እኛም የማናስተውለውን ታላቅ ነገር ያደርጋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔር አስደናቂ በሆነ ድምፁ ነጐድጓድን ያሰማል፤ እኛ ልንረዳው የማንችል ታላላቅ ነገሮችንም ያደርጋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ኀያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በድ​ምፁ ድንቅ አድ​ርጎ ያን​ጐ​ደ​ጕ​ዳል፤ ለእ​ን​ስ​ሳት በየ​ጊ​ዜው ምግ​ባ​ቸ​ውን ያዘ​ጋ​ጃል፥ የሚ​ተ​ኙ​በ​ት​ንም ጊዜ ያው​ቃሉ፤ በዚህ ሁሉ ልብህ አይ​ደ​ን​ግ​ጥ​ብህ፤ ሥጋ​ህም ልብ​ህም ከግ​ዘፉ አይ​ለ​ወ​ጥ​ብህ፤ እር​ሱም እኛ የማ​ና​ው​ቀ​ውን ታላቅ ነገር ያደ​ር​ጋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እግዚአብሔር በድምፁ ድንቅኛ ያንጐደጕዳል፥ እኛም የማናስተውለውን ታላቅ ነገር ያደርጋል።

参见章节 复制




ኢዮብ 37:5
18 交叉引用  

“የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምስጢር ልትለካ ትችላለህን? ወይስ ሁሉን ቻዩን አምላክ መርምረህ ትደርስበታለህን?


እነዚህ የሥራው ዳር ዳር ናቸው፤ ስለ እርሱ የሰማነው ምንኛ አነስተኛ ነው! የኀይሉንስ ነጐድጓድ ማን ሊያስተውል ይችላል?”


እነሆ፤ እግዚአብሔር ከአእምሯችን በላይ ታላቅ ነው! የዘመኑም ቍጥር ከመታወቅ ያልፋል።


“ኢዮብ ሆይ፤ ይህን ስማ፤ ቆም ብለህ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ዐስብ።


ደመናት ሚዛን ጠብቀው እንዴት እንደሚንሳፈፉ፣ በዕውቀቱ ፍጹም የሆነውን፣ የርሱን ድንቅ ሥራ ታውቃለህን?


ስሙ! የድምፁን ጩኸት፣ ከአፉም የሚወጣውን ጕርምርምታ፤


ከዚያም በኋላ የድምፁ ጩኸት ይመጣል፤ በድምፁም ግርማ ያንጐደጕዳል፤ ድምፁ በተሰማ ጊዜ፣ መብረቁን የሚከለክል የለም።


እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን? ድምፅህስ እንደ እርሱ ድምፅ ሊያንጐደጕድ ይችላልን?


እርሱ፣ የማይመረመሩ ድንቅ ነገሮች፣ የማይቈጠሩም ታምራት ያደርጋል።


የማይመረመሩ ድንቅ ነገሮችን፣ የማይቈጠሩ ታምራትንም ያደርጋል።


ፍላጻውን ሰድዶ በተናቸው፤ ታላቅ መብረቆቹንም ልኮ አወካቸው።


የእግዚአብሔር ድምፅ በውሆች ላይ ነው፤ የክብር አምላክ አንጐደጐደ፤ እግዚአብሔር በታላላቅ ውሆች ላይ አንጐደጐደ።


ሁሉንም ነገር በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ በሰዎችም ልብ ዘላለማዊነትን አኖረ፤ ይሁን እንጂ አምላክ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያደረገውን ማወቅ አይችሉም።


አታውቅምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፣ የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ነው። አይደክምም፤ አይታክትም፤ ማስተዋሉም በማንም አይመረመርም።


የእግዚአብሔር የጥበቡና የዕውቀቱ ባለጠግነት እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ አይመረመርም፤ ለመንገዱም ፈለግ የለውም!


የእግዚአብሔር ባሪያ የሆነውን የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፤ “ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ ሆይ፤ ሥራህ ታላቅና አስደናቂ ነው። የሕዝቦች ንጉሥ ሆይ፤ መንገድህ ጽድቅና እውነት ነው።


跟着我们:

广告


广告