Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 37:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ደመናት ሚዛን ጠብቀው እንዴት እንደሚንሳፈፉ፣ በዕውቀቱ ፍጹም የሆነውን፣ የርሱን ድንቅ ሥራ ታውቃለህን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ወይስ የደመናውን መንሳፈፍ፥ ወይስ በእውቀት ፍጹም የሆነውን ተአምራት አውቀሃልን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ደመናን በሕዋው ላይ የሚያንሳፍፈውንና ሁሉን የሚያውቀውን የአምላክን ድንቅ ሥራ ታውቃለህን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የደ​መ​ና​ትን ክፍ​ሎች፥ አስ​ፈሪ የሆ​ነ​ው​ንም የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችን አወ​ዳ​ደቅ ያው​ቃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ወይስ የደመናውን ሚዛን፥ ወይስ በእውቀት ፍጹም የሆነውን ተአምራት አውቀሃልን?

参见章节 复制




ኢዮብ 37:16
15 交叉引用  

ውሆችን በደመናዎቹ ይጠቀልላል፤ ክብደታቸውም ደመናዎቹን አይሸነቍርም።


ደመናትን እንዴት እንደሚዘረጋ፣ ከድንኳኑም እንዴት እንደሚያንጐደጕድ ሊረዳ የሚችል ማን ነው?


ቃሌ ሐሰት እንዳልሆነ አረጋግጣለሁ፤ በዕውቀቱ ፍጹም የሆነ ሰው ከአንተ ጋራ ነው።


“ኢዮብ ሆይ፤ ይህን ስማ፤ ቆም ብለህ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ዐስብ።


እግዚአብሔር ደመናትን እንዴት እንደሚቈጣጠር፣ መብረቁንም እንዴት እንደሚያባርቅ ታውቃለህን?


ምድር በደቡብ ነፋስ ጸጥ ባለች ጊዜ፣ ከሙቀት የተነሣ በልብስህ ውስጥ የምትዝለፈለፍ ሆይ፤


የእግዚአብሔር ድምፅ በሚያስደንቅ ሁኔታ ያንጐደጕዳል፤ እኛ የማናስተውለውንም ታላቅ ነገር ያደርጋል።


እርሱ፣ የማይመረመሩ ድንቅ ነገሮች፣ የማይቈጠሩም ታምራት ያደርጋል።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ብዙ ነው! ሁሉን በጥበብ ሠራህ፤ ምድርም በፍጥረትህ ተሞላች።


ጌታችን ታላቅ ነው፤ እጅግ ኀያልም ነው፤ ለጥበቡም ወሰን የለውም።


እኛም ከልጆቻቸው አንደብቀውም፤ የእግዚአብሔርን ምስጋና፣ ኀይሉንና ያደረገውን ድንቅ ሥራ፣ ለሚቀጥለው ትውልድ እንናገራለን።


እርሱ ከምድር ክበብ በላይ በዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ ሕዝቦቿም እንደ አንበጣ ናቸው። ሰማያትን እንደ ድባብ ይዘረጋቸዋል፤ እንደ መኖሪያ ድንኳንም ይተክላቸዋል።


跟着我们:

广告


广告