Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 36:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ሰዎች ከቤታቸው የሚወሰዱበትን፣ ሌሊት አትመኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ሰዎች ድንገት የሚሞቱበትን ሌሊትን አትመኛት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ሕዝቦች ከስፍራቸው የሚጠፉበት የጨለማ ጊዜ እንዲመጣ አትመኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በእ​ነ​ርሱ ፋንታ ወገ​ኖች እን​ዲ​ገቡ፥ ኀያ​ላን ሰዎ​ችን ሁሉ በሌ​ሊት አታ​ስ​ወጣ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ወገኖች ከስፍራቸው የሚወጡበትን ሌሊት አትመኝ።

参见章节 复制




ኢዮብ 36:20
16 交叉引用  

በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያን ሰፈር አንድ መቶ ሰማንያ ዐምስት ሺሕ ሰው ገደለ፤ ሰዎቹ ማለዳ ሲነሡ፤ ቦታው ሬሳ በሬሳ ነበር።


“ምነው መቃብር ውስጥ በሰወርኸኝ! ቍጣህም እስከሚያልፍ በሸሸግኸኝ! ምነው ቀጠሮ ሰጥተህ፣ ከዚያ በኋላ ባስታወስኸኝ!


እነርሱም እኩለ ሌሊት ላይ በድንገት ይሞታሉ፤ ሕዝብ ተንቀጥቅጦ ሕይወቱ ያልፋል፤ ኀያላኑም የሰው እጅ ሳይነካቸው ይወገዳሉ።


እርሱ ሥራቸውን ሁሉ ስለሚያውቅ፣ በሌሊት ይገለብጣቸዋል፤ እነርሱም ይደቅቃሉ።


ባለጠግነትህም ሆነ ብርቱ ጥረትህ ሁሉ፣ ችግር ውስጥ እንዳትገባ ሊረዳህ ይችላልን?


እግዚአብሔር አድቅቆ ያጠፋኝ ዘንድ፣ ምነው እጁ በተፈታ!


ስለዚህ እንዲህ ሆኖ ከመኖር፣ መታነቅና መሞትን እመርጣለሁ።


እኩለ ሌሊት ላይ እግዚአብሔር በግብጽ ምድር በዙፋን ላይ ከተቀመጠው ከፈርዖን የበኵር ልጅ ጀምሮ፣ በጨለማ እስር ቤት ውስጥ እስካለው እስረኛ የበኵር ልጅ ድረስ ያለውንና የእንስሳቱን በኵሮች ሁሉ ቀሠፋቸው።


ክፉዎች በክፋታቸው ይወድቃሉ፤ ጻድቃን ግን በሞት ጊዜ እንኳ መጠጊያ አላቸው።


ደመናት ውሃ ካዘሉ፣ በምድር ላይ ዝናብን ያዘንባሉ፤ ዛፍ ወደ ደቡብም ሆነ ወደ ሰሜን ቢወድቅ፣ በወደቀበት ቦታ በዚያ ይጋደማል።


በዚያ ሌሊት የባቢሎናውያን ንጉሥ ቤልሻዛር ተገደለ፤


“እግዚአብሔር ግን፣ ‘አንተ ሞኝ፤ ነፍስህን በዚህች ሌሊት ከአንተ ሊወስዱ ይፈልጓታል፤ እንግዲህ፣ ለራስህ ያከማቸኸው ለማን ይሆናል?’ አለው።


ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ትቶት በሄደው በዚህ አገልግሎትና በሐዋርያዊነት ቦታ ላይ ሹመው።”


跟着我们:

广告


广告