Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 36:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ታዝዘው ቢያገለግሉት፣ ቀሪ ዘመናቸውን በተድላ፣ ዕድሜያቸውንም በርካታ ይፈጽማሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከሰሙትና ካገለገሉት፥ ዕድሜአቸውን በብልጽግና፥ ዘመናቸውንም በተድላ ይፈጽማሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ለእግዚአብሔር ቢታዘዙና ቢያገለግሉ፥ ቀሪ ዘመናቸውን በብልጽግናና በደስታ ያሳልፋሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ቢሰ​ሙና ቢያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​ትም፥ ዕድ​ሜ​አ​ቸ​ውን በመ​ል​ካም፥ ዘመ​ና​ቸ​ው​ንም በተ​ድላ ይፈ​ጽ​ማሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ቢሰሙ ቢያገለግሉትም፥ ዕድሜአቸውን በልማት፥ ዘመናቸውንም በተድላ ይፈጽማሉ።

参见章节 复制




ኢዮብ 36:11
21 交叉引用  

ወደ እርሱም በጸለየ ጊዜ፣ በጭንቀት ልመናው ራርቶለት እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማው። ስለዚህ ወደ ኢየሩሳሌም፣ ወደ መንግሥቱም መለሰው፤ ምናሴም እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዐወቀ።


ልጆቻቸውን እንደ በግ መንጋ ያሰማራሉ፤ ሕፃናታቸውም ይቦርቃሉ።


ዕድሜያቸውን በተድላ ያሳልፋሉ፤ በሰላምም ወደ መቃብር ይወርዳሉ።


“ለእግዚአብሔር ተገዛ፤ ከርሱም ጋራ ሰላም ይኑርህ፤ በረከትም ታገኛለህ።


ወደ ሁሉን ቻይ አምላክ ብትመለስ ትጠገናለህ፤ ክፋትን ከድንኳንህ ብታርቅ፣


እግዚአብሔርም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን የኢዮብን ሕይወት ባረከ። እርሱም ዐሥራ አራት ሺሕ በጎች፣ ስድስት ሺሕ ግመሎች፣ አንድ ሺሕ ጥማድ በሬዎች፣ አንድ ሺሕ እንስት አህዮችም ነበሩት።


ዐመፅን አያደርጉም፤ ነገር ግን በመንገዱ ይሄዳሉ።


እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ይለዋልና፤ የዋሃንንም በማዳኑ ውበት ያጐናጽፋል።


የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ።


የሚያዳምጠኝ ሁሉ ግን በሰላም ይኖራል፤ ክፉን ሳይፈራ ያለ ሥጋት ይቀመጣል።”


ዕሺ ብትሉ፣ ብትታዘዙም የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤


አሁንም መንገዳችሁንና ሥራችሁን አስተካክሉ፣ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ታዘዙ። እግዚአብሔርም በእናንተ ላይ ለማምጣት የተናገረውን ክፉ ነገር ይተዋል።


ነገር ግን ድምፄን ስሙ፤ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ፤ መልካም እንዲሆንላችሁም፣ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ ብዬ አዘዝኋቸው።


ነገር ግን የኀጢአት ባሮች የነበራችሁ ቢሆንም፣ ለተሰጣችሁለት ትምህርት በሙሉ ልብ የታዘዛችሁ በመሆናችሁ፣ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤


ስትጨነቅና ይህ ሁሉ ነገር ሲደርስብህ ያን ጊዜ፣ በኋለኞቹ ዘመናት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ትመለሳለህ፤ ትታዘዝለታለህም።


የአካል ብቃት ልምምድ ለጥቂት ነገር ይጠቅማልና፤ ለእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ራስን ማሠልጠን ግን ለአሁኑም ሆነ ለሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለሁለቱም ይጠቅማል።


አብርሃም ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም፣ ዕሺ ብሎ ሄደ።


በምድርም ላይ በምቾትና በመቀማጠል ኖራችኋል፤ ለዕርድ ቀን ልባችሁን አወፍራችኋል።


ለራሷ ክብርና ምቾት የሰጠችውን ያህል፣ ሥቃይና ሐዘን ስጧት፤ በልቧም እንዲህ እያለች ትመካለች፤ ‘እንደ ንግሥት ተቀምጬአለሁ፤ መበለትም አይደለሁም፤ ከቶም አላዝንም፤’


跟着我们:

广告


广告