Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 36:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ተግሣጽን እንዲሰሙ ያደርጋቸዋል፤ ከክፋታቸውም እንዲመለሱ ያዝዛቸዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጆሮአቸውን ለተግሣጽ ይከፍተዋል፥ ከክፋትም ይመለሱ ዘንድ ያዝዛቸዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ተግሣጽን እንዲሰሙ ጆሮአቸውን ይከፍትላቸዋል፤ ከክፉ ሥራቸውም ተመልሰው ንስሓ እንዲገቡ ያዛቸዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ጻድ​ቃ​ንን ግን ይሰ​ማ​ቸ​ዋል፥ ከኀ​ጢ​አ​ትም ይመ​ለሱ ዘንድ ያዝ​ዛ​ቸ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ጆሮአቸውን ለተግሣጽ ይከፍተዋል፥ ከኃጢአትም ይመለሱ ዘንድ ያዝዛቸዋል።

参见章节 复制




ኢዮብ 36:10
24 交叉引用  

ይህም ሆኖ እግዚአብሔር፣ “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ አባቶቻችሁ እንዲፈጽሙት ባዘዝኋቸው ሕግ ሁሉ መሠረት እንዲሁም በአገልጋዮቼ በነቢያት አማካይነት ለእናንተ ባስተላለፍሁት ሕግ መሠረት፣ ትእዛዜንና ሥርዐቴን ጠብቁ” ብሎ በነቢያቱና በባለራእዮች ሁሉ እስራኤልንና ይሁዳን አስጠንቅቆ ነበር።


ነገር ግን የሚሠቃዩትን ከሥቃያቸው ያድናቸዋል፤ በመከራቸውም ውስጥ ይናገራቸዋል።


ከመከራ ይልቅ መርጠኸዋልና፣ ወደ ክፋት እንዳትመለስ ተጠንቀቅ።


መሥዋዕትንና ቍርባንን አልፈለግህም፤ ጆሮዎቼን ግን ከፈትህ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትን፣ የኀጢአትንም መሥዋዕት አልሻህም።


የተቤዠህ፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣ የሚበጅህ ምን እንደ ሆነ የማስተምርህ፣ መሄድ በሚገባህ መንገድ የምመራህ ነኝ።


አልሰማህም ወይም አላወቅህም፤ ጆሮህ ከጥንት የተከፈተ አልነበረም፤ አንተ አታላይ እንደ ነበርህ፣ ከልጅነትህ ጀምሮ ዐመፀኛ መባልህን ዐውቄአለሁና።


ልዑል እግዚአብሔር ጆሮዬን ከፍቶታል፤ እኔም ዐመፀኛ አይደለሁም፤ ወደ ኋላም አላፈገፈግሁም።


እስራኤል ሆይ፤ በኀጢአትህ ምክንያት ስለ ወደቅህ፣ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ።


ነገር ግን ሰውም እንስሳም ማቅ ይልበስ፤ ሁሉም አጥብቆ ወደ እግዚአብሔር ይጩኽ፤ ሰዎችም ሁሉ ክፉ መንገዳቸውንና የግፍ ሥራቸውን ይተዉ።


እኔም ከተማዪቱን፣ ‘በርግጥ ትፈሪኛለሽ፤ ዕርምትም ትቀበያለሽ’ አልኋት፤ ስለዚህ መኖሪያዋ አይጠፋም፤ ቅጣቴም ሁሉ በርሷ ላይ አይደርስም። እነርሱ ግን በሚያደርጉት ሁሉ፣ ክፋትንም በመፈጸም እየተጉ ሄዱ።”


እንግዲህ ለንስሓ የሚገባ ፍሬ አፍሩ፤


ከሚያዳምጡትም ሴቶች መካከል ልድያ የምትባል አንዲት ሴት ነበረች፤ እርሷም እግዚአብሔርን የምታመልክና ከትያጥሮን ከተማ የመጣች የቀይ ሐር ነጋዴ ነበረች። ጌታም፣ ጳውሎስ የሚናገረውን በማስተዋል ትሰማ ዘንድ ልቧን ከፈተላት።


ቀደም ሲል እግዚአብሔር እንዲህ ያለውን አለማወቅ በትዕግሥት ዐልፏል፤ አሁን ግን በየቦታው ያሉ ሰዎች ሁሉ ንስሓ እንዲገቡ ያዝዛል።


እንግዲህ ኀጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሓ ግቡ፤ ከመንገዳችሁም ተመለሱ፤ ከጌታም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል፤


ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች እጃችሁን አንጹ፤ እናንተ በሁለት ሐሳብ የምትዋልሉ ልባችሁን አጥሩ።


跟着我们:

广告


广告