Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 34:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ሁሉም የእጁ ሥራ ስለ ሆኑ፣ እርሱ ለገዦች አያደላም፤ ባለጠጋውንም ከድኻው አብልጦ አይመለከትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እነርሱ ሁሉ የእጁ ሥራ ናቸውና ለአለቆች አያደላም፥ ሀብታሙንም ሰው ከድሀው ይበልጥ አይመለከትም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ሁሉም የእጁ ሥራዎች ስለ ሆኑ፤ እርሱ ለመኳንንቱ አያደላም ባለጸጋውን ከድኻው አይለይም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እርሱ ግን የክ​ቡ​ርን ሰው ፊት አያ​ፍ​ርም። ለታ​ላ​ቁም ክብር መስ​ጠ​ትን አያ​ው​ቅም፥ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አይ​ሸ​ሽም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እነርሱ ሁሉ የእጁ ሥራ ናቸውና በአለቆች ፊት አያደላም፥ ባለጠጋውንም ሰው ከድሀው ይበልጥ አይመለከትም።

参见章节 复制




ኢዮብ 34:19
28 交叉引用  

አሁንም እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ፍርድ ማጣመም፣ አድልዎ ማድረግና መማለጃ መቀበል ስለሌለ ተጠንቅቃችሁ ፍረዱ።”


የክፉዎችን ዕቅድ በደስታ እየተቀበልህ፣ እኔን ግን ስታስጨንቀኝ፣ የእጅህንም ሥራ ስታዋርድ ደስ ይልሃልን?


ካህናትን ከክህነታቸው ያዋርዳል፤ ለዘመናት የተደላደሉትንም ይገለብጣል።


የተከበሩትን ውርደት ያከናንባል፤ ብርቱዎችንም ትጥቅ ያስፈታል።


በስውር አድልዎ ብታደርጉ፣ በርግጥ እርሱ ይገሥጻችኋል።


ለርሱ ታደላላችሁን? ለእግዚአብሔር ጥብቅና ልትቆሙ ነውን?


እኔን በማሕፀን ውስጥ የፈጠረኝ እነርሱን የፈጠረ አይደለምን? በሆድ ውስጥ የሠራንስ እርሱ ራሱ አይደለምን?


ለማንም አላደላም፤ ሰውንም አላቈላምጥም።


ነገሥታትን ‘ምናምንቴ ናችሁ፣’ መኳንንትንም፣ ‘ክፉዎች ናችሁ’ የሚላቸው እርሱ አይደለምን?


ባለጠግነትህም ሆነ ብርቱ ጥረትህ ሁሉ፣ ችግር ውስጥ እንዳትገባ ሊረዳህ ይችላልን?


ለሕይወታችሁ ማስተስረያ እንዲሆን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት በምታቀርቡበት ጊዜ ባለጠጋው ከግማሽ ሰቅል በላይ፣ ድኻውም አጕድሎ አይስጥ።


ድኾችን የሚያስጨንቅ ፈጣሪያቸውን ይንቃል፤ ለተቸገሩ የሚራራ ሁሉ ግን አምላክን ያከብራል።


ባለጠጋና ድኻ የሚጋሩት ነገር፣ እግዚአብሔር የሁላቸውም ፈጣሪ መሆኑ ነው።


በአገር ውስጥ ድኻ ተጨቍኖ፣ ፍትሕ ተጓድሎ፣ መብትም ተረግጦ ብታይ፣ እንደነዚህ ባሉ ነገሮች አትደነቅ፤ ምክንያቱም አንዱን አለቃ የበላዩ ይመለከተዋል፤ በእነዚህ በሁለቱም ላይ ሌሎች ከፍ ያሉ አሉ።


እግዚአብሔር፣ ከአለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋራ እንዲህ ሲል ይፋረዳል፤ “የወይኔን ቦታ ያጠፋችሁ እናንተ ናችሁ፤ ከድኾች የዘረፋችሁትም በቤታችሁ ይገኛል፤


“ ‘ፍርድ አታዛቡ፤ ለድኻው አታድላለት፤ ለትልቁም ሰው ልዩ አክብሮት አትስጥ፤ ለብርቱው አታድላ፤ ነገር ግን ለባልንጀራህ በጽድቅ ፍረድ።


ጴጥሮስም እንዲህ ሲል መናገር ጀመረ፤ “እግዚአብሔር ለማንም እንደማያዳላ በእውነት ተረድቻለሁ፤


እግዚአብሔር ለማንም አያደላምና።


እግዚአብሔር የተከበረውን እንደሌለ ለማድረግ፣ በዚህ ዓለም ዝቅ ያለውንና የተናቀውን ነገር፣ ቦታም ያልተሰጠውን ነገር መረጠ፤


ዋነኛ መስለው ስለሚታዩት ሰዎች ማንነት እኔን አይገደኝም፤ እግዚአብሔር የሰውን ፊት አይቶ አያደላም፤ እነዚህም ሰዎች ለመልእክቴ የጨመሩልኝ ነገር የለም።


እናንተም ጌቶች ሆይ፤ ለባሮቻችሁ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የእነርሱም፣ የእናንተም ጌታ የሆነው በሰማይ እንዳለ፣ የሰውንም ፊት አይቶ እንደማያደላ ታውቃላችሁና አታስፈራሯቸው።


አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፣ የጌቶች ጌታ ታላቅ አምላክ፣ ኀያልና የሚያስፈራ፣ አድልዎ የማያደርግ፣ መማለጃም የማይቀበል ነውና።


በደለኛውም የእጁን ያገኛል፤ አድልዎም የለም።


ስለዚህ ከቶ የማይናወጥ መንግሥት ስለምንቀበል እግዚአብሔርን እናመስግን፤ ደግሞም ደስ በሚያሠኘው መንገድ በአክብሮትና በፍርሀት እናምልከው፤


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለጠጋ እንዲሆኑና እርሱን ለሚወድዱም ተስፋ የተሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


ለሰው ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደየሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ፣ በዚህ ምድር በእንግድነት ስትኖሩ በፍርሀት ኑሩ።


跟着我们:

广告


广告