Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 33:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ነፍሱ ወደ ጕድጓድ፣ ሕይወቱም ወደ ሞት መልእክተኞች ትቀርባለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ነፍሱ ወደ ጉድጓዱ፥ ሕይወቱም ወደሚገድሉአት ቀርባለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ሕይወቱ አልፎ ነፍሱ ወደ ሙታን ዓለም ለመውረድ ተቃርባለች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሰው​ነቱ ለሞት፥ ሕይ​ወ​ቱም ወደ ሲኦል ቀር​ባ​ለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ነፍሱ ወደ ጕድጓዱ፥ ሕይወቱም ወደሚገድሉአት ቀርባለች።

参见章节 复制




ኢዮብ 33:22
17 交叉引用  

የእግዚአብሔር መልአክ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፣ የደረሰው ጕዳት እግዚአብሔርን ስላሳዘነው፣ ሕዝቡን የሚቀሥፈውን መልአክ “በቃ! እጅህን መልስ” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።


የሚያስደነግጥ ድምፅ በጆሮው ላይ ይጮኻል፤ በሰላም ጊዜ ቀማኞች አደጋ ያደርሱበታል።


መንፈሴ ደክሟል፣ ዘመኔ ዐጥሯል፤ መቃብርም ተዘጋጅቶልኛል።


ነፍሱን ከጕድጓድ፤ ሕይወቱንም ከሰይፍ ጥፋት ያድናል።


ነፍሴ ወደ ጕድጓድ እንዳትወርድ፣ ታድጓታል፤ በሕይወትም ሆኜ ብርሃን አያለሁ።’


ሕይወቴ ትንፋሽ ያህል እንደ ሆነች ዐስብ፤ ዐይኔም ከእንግዲህ ደስታን አያይም።


ሰውነታቸው የምግብ ዐይነት ሁሉ ተጸየፈች፤ ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ።


ከሰዎች ተግባር፣ በከንፈርህ ቃል፣ ከዐመፀኞች መንገድ፣ ራሴን ጠብቄአለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፤ ወደ ጕድጓድ ከመውረድም መልሰህ ሕያው አደረግኸኝ።


እግዚአብሔር ግብጻውያንን ለመቅሠፍ በምድሪቱ ላይ በሚያልፍበት ጊዜ በጕበኑና በመቃኑ ላይ ያለውን ደም ሲያይ ያን ደጃፍ ዐልፎ ይሄዳል፤ ቀሣፊውም ወደ ቤታችሁ ገብቶ እንዳይገድላችሁ ይከለክለዋል።


እኔ፣ “በዕድሜዬ እኩሌታ፣ በሲኦል ደጆች ማለፍ አለብኝን? የቀረውንስ ዘመኔን ልነጠቅ ይገባልን?” አልሁ።


ሄሮድስም ለእግዚአብሔር ክብር ስላልሰጠ የጌታ መልአክ ወዲያው መታው፤ በትልም ተበልቶ ሞተ።


ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳጕረመረሙና በአጥፊው እንደ ጠፉ፣ አታጕረምርሙ።


በላያቸው ንጉሥ ነበራቸው፤ እርሱም የጥልቁ ጕድጓድ መልአክ ነው፤ ስሙም በዕብራይስጥ “አብዶን”፣ በግሪክ ደግሞ “አጶልዮን” ይባላል።


“እግዚአብሔር ይገድላል፤ ያድናልም፤ ወደ መቃብር ያወርዳል፤ ያወጣልም።


跟着我们:

广告


广告