Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 32:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስለዚህ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ እንዲህ አለ፤ “እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፤ እናንተ ግን አዛውንቶች ናችሁ፤ ከዚህም የተነሣ የማውቀውን ለመናገር አልደፈርሁም፤ ፈርቼ ዝም አልሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ተናገረ፤ እንዲህም አለ፦ “እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፥ ስለዚህም ሰጋሁ፥ የማውቀውን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈራሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ቡዛዊው የባራኪ ልጅ ኤሊሁ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ በዕድሜዬ ከእናንተ ያነስኩ በመሆኔና እናንተም አዛውንት በመሆናችሁ፥ ኀፍረትና ፍርሀት ተሰምቶኝ ሐሳቤን ሳልገልጥ እስከ አሁን ቈይቼ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የቡ​ዛ​ዊው የባ​ር​ክ​ኤል ልጅ ኤል​ዩ​ስም መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እኔ በዕ​ድ​ሜዬ ታናሽ ነኝ፥ እና​ንተ ግን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ናችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ዕው​ቀ​ቴን እገ​ል​ጥ​ላ​ችሁ ዘንድ ፈርቼ ዝም አልሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ተናገረ እንዲህም አለ፦ እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፥ ስለዚህም ሰጋሁ፥ እውቀቴን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈራሁ።

参见章节 复制




ኢዮብ 32:6
14 交叉引用  

ጥበብ ያለው በአረጋውያን ዘንድ አይደለምን? ማስተዋልስ ረዥም ዕድሜ ባላቸው ዘንድ አይገኝምን?


በዕድሜ ከአባትህ የሚበልጡ፣ የሸበቱ ሽማግሌዎች ከእኛ ጋራ አሉ።


“ለመሆኑ ከሰው ሁሉ ቀድመህ የተወለድህ አንተ ነህን? ወይስ ከኰረብቶች በፊት ተገኝተሃል?


ከራም ወገን የሆነው፣ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ግን ኢዮብ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ጻድቅ ስላደረገ እጅግ ተቈጣው።


ነገር ግን ኤሊሁ እነዚህ ሦስቱ የሚሉትን ባጡ ጊዜ ቍጣው ነደደ።


ኤሊሁ በመቀጠል እንዲህ አለ፤


ኤሊሁ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤


ኤሊሁ በመቀጠል እንዲህ አለ፤


“ ‘ዕድሜው ለገፋ ተነሥለት፤ ሽማግሌውን አክብር፤ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


ለእያንዳንዱ የሚገባውን ስጡ፤ ግብር ከሆነ ግብርን፣ ቀረጥ ከሆነም ቀረጥን፣ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፣ ክብር ለሚገባውም ክብርን ስጡ።


አረጋዊውን ሰው እንደ አባትህ ቈጥረህ ምከረው እንጂ በኀይለ ቃል አትናገረው። ወጣት ወንዶችን እንደ ወንድሞች ተቀበላቸው፤


እንዲሁም ወጣት ወንዶች ራሳቸውን እንዲገዙ ምከራቸው።


ጕልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርስ በመከባበር ትሕትናን ልበሱ፤ ምክንያቱም፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።”


跟着我们:

广告


广告