Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 31:35 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 “ምነው የሚሰማኝ ባገኝ! የመከላከያ ፊርማዬ እነሆ፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ይመልስልኝ፤ ከሳሼም ክሱን በጽሑፍ ያቅርብ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 የሚያዳምጠኝ ምነው በኖረልኝ! እነሆ የእጄ ምልክት፥ ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ፥ ከባላጋራዬ የተጻፈው የክስ ጽሑፍ ምነው በተገኘልኝ!

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 “ምነው የሚሰማኝ ባገኘሁ! መከላከያዬን አቀርባለሁ፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ይመልስልኝ! ምነው ከሳሼም የክሱን ዝርዝር በጽሑፍ አቅርቦልኝ ባየሁት!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 የሚ​ያ​ደ​ም​ጠ​ኝን ማን በሰ​ጠኝ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እጅ አል​ፈ​ራሁ እንደ ሆነ፥ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ር​ድ​ብኝ የክስ ጽሑፍ ምነው በኖ​ረኝ!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 የሚያዳምጠኝ ምነው በኖረልኝ! እነሆ የእጄ ምልክት፥ ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ፥ ከባላጋራዬ የተጻፈው የክስ ጽሑፍ ምነው በተገኘልኝ!

参见章节 复制




ኢዮብ 31:35
22 交叉引用  

ቃሌን በጥንቃቄ አድምጡ፤ እኔ የምለውንም ጆሯችሁ በሚገባ ይስማ፤


ፊትህን ለምን ትሰውራለህ? እንደ ጠላትህስ ለምን ትቈጥረኛለህ?


ነገር ግን ከሁሉን ቻይ አምላክ ጋራ መነጋገር እፈልጋለሁ፤ ከእግዚአብሔርም ጋራ መዋቀሥ እሻለሁ።


“አምላክ ሆይ፤ አንተ ተያዥ ሁነኝ፤ ከአንተ ሌላ ዋስ የሚሆነኝ ማን አለ?


ቍጣው በላዬ ነድዷል፤ እንደ ጠላቱም ቈጥሮኛል።


“ ‘ተበደልሁ’ ብዬ ብጮኽ ማንም አይመልስልኝም፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ባሰማም፣ ፍትሕ አላገኝም።


“ጠላቴ እንደ በደለኛ፣ ባላንጣዬም እንደ ክፉ ይሁን።


“አምላክ ሆይ፤ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ ነገር ግን አልመለስህልኝም፤ በፊትህም ቆምሁ፤ አንተ ግን ዝም አልኸኝ።


“የተጐዳ ሰው ተጨንቆ ድረሱልኝ ብሎ ሲጮኽ፣ በርግጥ ክንዱን የሚያነሣበት ማንም የለም።


በፀሓይ አይደለም እንጂ፣ ጠቋቍሬ እዞራለሁ፤ በጉባኤ መካከል ቆሜ ለርዳታ እጮኻለሁ።


በርግጥ ትከሻዬ ላይ በደረብሁት፣ እንደ አክሊልም ራሴ ላይ በደፋሁት ነበር።


በእግዚአብሔር ፊት እኔም እንደ አንተው ነኝ፤ የተፈጠርሁትም ደግሞ ከዐፈር ነው።


ጕዳይህን ፊቱ አቅርበህ፣ ብዙ ጠብቀኸው፣ ግን እንዳላየኸው ስትናገር፣ ታዲያ፣ አንተን እንዴት ይስማህ!


“ከሁሉን ቻይ አምላክ ጋራ ተከራክሮ የሚረታው አለን? እግዚአብሔርን የሚወቅሥ እርሱ መልስ ይስጥ!”


እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ነቀፋ እንደ መሆኔ፣ አንተው ፍረድልኝ። ወዲያ ወዲህ ሳልልም፣ በእግዚአብሔር ታምኛለሁ።


“የከሰሰህ ባላጋራህ እንዳያስፈርድብህ፣ ዳኛውም ለአገልጋዩ አሳልፎ እንዳይሰጥህ፣ ወደ ወህኒ እንዳትጣል፣ በመንገድ ላይ ሳለህ ከባላጋራህ ጋራ ፈጥነህ ተስማማ።


跟着我们:

广告


广告