Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 30:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ለሕያዋን ሁሉ ወደ ተመደበው ስፍራ፣ ወደ ሞት እንደምታወርደኝ ዐውቃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ለሞት፥ ሕያዋንም ሁሉ ለሚሰበሰቡበት ቤት አሳልፈህ እንደምትሰጠኝ አውቄአለሁና።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የሰው ሁሉ ዕድል ፈንታ ለሆነው ለሞት አሳልፈህ እንደምትሰጠኝ ዐውቃለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ሞት እን​ደ​ሚ​ያ​ጠ​ፋኝ አው​ቃ​ለ​ሁና ለሟ​ችም ሁሉ ማደ​ሪ​ያው ምድር ናትና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ለሞት ሕያዋንም ሁሉ ለሚሰበሰቡበት ቤት አሳልፈህ እንደምትሰጠኝ አውቄአለሁና።

参见章节 复制




ኢዮብ 30:23
12 交叉引用  

ከምድር ስለ ተገኘህ፣ ወደ መጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ እንጀራህን በፊትህ ላብ ትበላለህ፤ ዐፈር ነህና ወደ ዐፈር ትመለሳለህ።”


በመሬት ላይ የፈሰሰ ውሃ እንደማይታፈስ ሁሉ፣ እኛም እንደዚሁ እንሞታለን፤ እግዚአብሔር ግን ከአገር የተሰደደ ሰው ከርሱ እንደ ራቀ በዚያው እንዳይቀር የሚመለስበትን ሁኔታ ያመቻቻል እንጂ ሕይወቱ እንድትጠፋ አይፈቅድም።


“እጅህ አበጀችኝ፤ ሠራችኝም፤ መልሰህ ደግሞ ታጠፋኛለህን?


የሰው ዕድሜ አስቀድሞ የተወሰነ ነው፤ የወራቱንም ብዛት ወስነህ አስቀምጠሃል፤ ሊያልፈው የማይችለውንም ገደብ አኖርህለት።


የሸለቈው ዐፈር ምቹ ይሆንለታል፤ ሰው ሁሉ ይከተለዋል፤ ስፍር ቍጥር የሌለው ሕዝብ በፊቱ ይሄዳል።


ትንሹም ትልቁም በዚያ ይገኛል፤ ባሪያው ከጌታው ነጻ ወጥቷል።


ሁሉም አንድ ነው፤ ‘እርሱ ጻድቁንና ኀጥኡን ያጠፋል’ የምለውም ለዚህ ነው።


ሰው ነፋስን መቈጣጠር አይችልም፤ በዕለተ ሞቱም ላይ ሥልጣን ያለው ማንም የለም፤ በጦርነት ጊዜ ማንም ከግዴታ ነጻ እንደማይሆን፣ ክፋትም የሚለማመዷትን አትለቃቸውም።


ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን ምንም አያውቁምና፤ መታሰቢያቸው ይረሳል፤ ምንም ዋጋ የላቸውም።


ሰው አንድ ጊዜ ሊሞት ከዚያም በኋላ በፍርድ ፊት ሊቆም ተወስኖበታል።


“እነሆ፤ አሁን የምድርን ሁሉ መንገድ ልሄድ ነው፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ መልካም ተስፋ ሁሉ አንዲቱን እንኳ እንዳላስቀረባችሁ፣ በፍጹም ልባችሁ በፍጹም ነፍሳችሁ ታውቃላችሁ፤ አንዱም ሳይቀር ሁሉም ተፈጽሟል።


跟着我们:

广告


广告