ኢዮብ 29:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም18 “እኔም በልቤ እንዲህ አልሁ፤ ‘ዘመኔ እንደ አሸዋ በዝቶ፣ በቤቴ ተደላድዬ እሞታለሁ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 እኔም፦ ‘በልጆቼ መካከል በክብር እሞታለሁ፥ ዕድሜዬንም እንደ አሸዋ አበዛለሁ፥’ እል ነበር፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 “ ‘ዕድሜዬ እንደ አሸዋ በዝቶ፥ በቤቴ እንዳለሁ በክብር እሞታለሁ’ ብዬ ነበር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 እኔም እንደምሸመግልና እንደማረጅ፥ እንደ ረዥም ዘንባባም ረዥም ዘመን እንደምኖር፥ እንደ አሸዋም ዘመኔን እንደማበዛ ዐሰብሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 እኔም አልሁ፦ በልጆቼ መካከል እሞታለሁ፥ ዕድሜዬንም እንደ አሸዋ አበዛለሁ፥ 参见章节 |