ኢዮብ 29:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ጽድቅን እንደ ልብስ ለበስሁ፤ ፍትሕም መጐናጸፊያዬና ጥምጥሜ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ጽድቅን ለበስሁ እርሷም ለበሰችኝ፥ ፍርዴም እንደ ካባና እንደ ቆብ ነበረ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ጽድቅን እንደ ልብስ ለበስኳት፤ ትክክለኛ ፍርድንም እንደ ካባ ደረብኳት፤ እንደ ቆብም ደፋኋት። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ጽድቅን ለበስሁ፥ ቅንነትንም እንደ መጎናጸፊያ ተሸለምሁ፤ ፍርድንም እንደ ኩፋር ተቀዳጀኋት 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ጽድቅን ለበስሁ እርስዋም ለበሰችኝ፥ ፍርዴም እንደ መጐናጸፊያና እንደ ኵፋር ነበረ። 参见章节 |