Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 24:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በምድረ በዳ እንዳሉ የሜዳ አህዮች፣ ድኾች ምግብ ፍለጋ ይራወጣሉ፤ ከበረሓው ምድር ለልጆቻቸው ምግብ ይሻሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እነሆ፥ በምድረ በዳ እንዳሉ እንደ ሜዳ አህዮች፥ መብልን ፈልገው ወደ ሥራቸው ይወጣሉ፥ ምድረ በዳውም ለልጆቻቸው መብልን ይሰጣቸዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ድኾች በበረሓ እንዳሉ የሜዳ አህዮች ለልጆቻቸው ምግብ ለመፈለግ ወጥተው ይንከራተታሉ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እነሆ፥ በም​ድረ በዳ እን​ዳሉ እንደ ሜዳ አህ​ዮች ሆኑ። ስለ እኔም ሥራ​ቸ​ውን ትተው ይወ​ጣሉ፤ መብል፦ ከል​ጅ​ነ​ታ​ቸው ጀምሮ ይጥ​ማ​ቸ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እነሆ፥ በምድር በዳ እንዳሉ እንደ ሜዳ አህዮች፥ መብልን ፈልገው ወደ ሥራቸው ይወጣሉ፥ ምድረ በዳውም ለልጆቻቸው መብልን ይሰጣቸዋል።

参见章节 复制




ኢዮብ 24:5
16 交叉引用  

እርሱም እንደ ዱር አህያ ይሆናል፤ እጁንም ባገኘው ሰው ሁሉ ላይ ያነሣል፤ ያገኘውም ሁሉ እጁን ያነሣበታል፤ ከወንድሞቹ ሁሉ ጋራ እንደ ተጣላ ይኖራል።”


በሰይፍ ትኖራለህ፤ የወንድምህም አገልጋይ ትሆናለህ። አምርረህ በተነሣህ ጊዜ ግን፣ ቀንበሩን ከጫንቃህ ላይ፣ ወዲያ ትጥላለህ።”


የቀማኞች ድንኳን አይታወክም፤ አምላካቸውን በእጃቸው ይዘው እየዞሩም፣ እግዚአብሔርንም እያስቈጡ በሰላም ይኖራሉ።


ቀኑ ሲመሽ፣ ነፍሰ ገዳይ ይነሣል፤ ችግረኞችንና ድኾችን ይገድላል፤ በሌሊትም እንደ ሌባ ያደባል፤


ከሜዳ መኖ ይሰበስባሉ፤ ከክፉዎች የወይን ቦታም ይቃርማሉ።


ከእሾኽ መካከል እንኳ አውጥቶ፣ ራብተኛ ሰብሉን ይበላበታል፤ ጥማተኛም ሀብቱን ይመኝበታል።


ሰውም ወደ ሥራው ይሄዳል፤ እስኪመሽም በተግባሩ ላይ ይሰማራል።


ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፤ ሰውን ካላሰናከሉ እንቅልፍ በዐይናቸው አይዞርም።


በምድረ በዳ እንደ ለመደች፣ በፍትወቷ ነፋስን እንደምታነፈንፍ፣ የሜዳ አህያ ነሽ፤ ከመጐምጀቷ ማን ሊገታት ይችላል? ለሚፈልጓት ሁሉ ያለ ምንም ድካም በፍትወቷ ወራት በቀላሉ ትገኝላቸዋለች።


ልባቸው እንደ ምድጃ የጋለ ነው፤ በተንኰል ይቀርቡታል፤ ቍጣቸው ሌሊቱን ሙሉ ይጤሳል፤ እንደሚነድድም እሳት በማለዳ ይንበለበላል።


ለብቻው እንደሚባዝን የዱር አህያ፣ ወደ አሦር ሄደዋልና፤ ኤፍሬም በእጅ መንሻ ወዳጅ አበጀ።


ክፉ ለመሥራት ለሚያቅዱ፣ በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ሲነጋ በማለዳ ይፈጽሙታል፤ የሚያደርጉበት ኀይል በእጃቸው ነውና።


ሹሞቿ የሚያገሡ አንበሶች፣ ገዦቿ ለነገ የማይሉ፣ የምሽት ተኵላዎች ናቸው።


አይሁድም ኢየሱስን ከቀያፋ ወደ ሮማዊው ገዥ ግቢ ይዘውት ሄዱ፤ ጊዜውም ማለዳ ነበር። አይሁድም ፋሲካን መብላት እንዲችሉ፣ ላለመርከስ ወደ ገዥው ግቢ አልገቡም።


በነጋም ጊዜ፣ አይሁድ ተሰብስበው በማሤር ጳውሎስን እስኪገድሉ ድረስ እህል ውሃ ላለመቅመስ ተማማሉ። በዚህ ሤራ


跟着我们:

广告


广告