Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 21:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እናገለግለው ዘንድ፣ ሁሉን ቻይ አምላክ ማን ነው? ወደ እርሱ ብንጸልይስ ምን እናገኛለን?’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እናመልከውስ ዘንድ ሁሉን የሚችል አምላክ ማን ነው? ወይስ ወደ እርሱ ብንጸልይ ምን ይጠቅመናል?” ይላሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ‘እናመልከው ዘንድ ሁሉን ቻይ አምላክ ማነው? ወደ እርሱስ መጸለይ ምን ይጠቅመናል?’ ይላሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እን​ገ​ዛ​ለ​ትስ ዘንድ እርሱ ምን ይች​ላል? ወይስ ወደ እርሱ ብን​ቀ​ርብ ምን ይጠ​ቅ​መ​ናል?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እናመልከውስ ዘንድ ሁሉን የሚችል አምላክ ማን ነው? ወይስ ወደ እርሱ ብንጸልይ ምን ይጠቅመናል? ይላሉ።

参见章节 复制




ኢዮብ 21:15
16 交叉引用  

እግዚአብሔርንም ‘አትድረስብን! ሁሉን ቻይ አምላክም ምን ያደርግልናል?’ አሉ።


አንተ ጻድቅ ብትሆን ሁሉን ቻዩን አምላክ ምን ደስ ታሠኘዋለህ? መንገድህ ያለ ነቀፋ ቢሆንስ የሚተርፈው ምንድን ነው?


‘እግዚአብሔርን ለማስደሰት መሞከር፣ ለሰው አንዳች አይጠቅምም’ ብሏልና።


ደግሞ ‘ያገኘሁት ጥቅም ምንድን ነው? ኀጢአት ባለመሥራቴስ ምን አተረፍሁ?’ ብለህ ጠይቀኸዋል።


እነዚህም፣ “በአንደበታችን እንረታለን፤ ከንፈራችን የእኛ ነው፤ ጌታችንስ ማነው?” የሚሉ ናቸው።


ለካ ልቤን ንጹሕ ያደረግሁት በከንቱ ነው፤ እጄንም በየዋህነት የታጠብሁት በከንቱ ኖሯል!


ፈርዖንም “እንድታዘዘውና እስራኤልን እንድለቅለት ለመሆኑ ይህ እግዚአብሔር ማነው? እግዚአብሔርን አላውቅም፤ እስራኤልንም አልለቅም” አለ።


አለዚያ ግን ያለ ልክ እጠግብና እክድሃለሁ፤ ‘እግዚአብሔር ማን ነው?’ እላለሁ፤ ወይም ድኻ እሆንና እሰርቃለሁ፤ የአምላኬንም ስም አሰድባለሁ።


ከዚህ መንገድ ፈቀቅ በሉ፤ ከጐዳናውም ራቁ፤ ከእስራኤል ቅዱስ ጋራ ፊት ለፊት አታጋጥሙን!”


በጨለማ ምድር፣ በምስጢር አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብም ዘር፣ ‘በከንቱ ፈልጉኝ’ አላልሁም። እኔ እግዚአብሔር ጽድቅን እናገራለሁ፤ ትክክለኛውንም ነገር ዐውጃለሁ።


መኖሪያህ በሽንገላ መካከል ነው፤ ከሽንገላቸውም የተነሣ ሊያውቁኝ አልፈቀዱም፤” ይላል እግዚአብሔር።


ካበላኋቸው በኋላ ጠገቡ፤ በጠገቡ ጊዜ ታበዩ፤ ከዚያም ረሱኝ።


“እንዲህም ብላችኋል፤ ‘እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፤ እርሱ የሚፈልገውን ሁሉ በማድረግና በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ፊት ሐዘንተኞች ሆነን በመመላለስ ምን ተጠቀምን?


“ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ በሩም ይከፈትላችኋል።


እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ለምኑ ትቀበላላችሁ፤ ደስታችሁም ሙሉ ይሆናል።


跟着我们:

广告


广告