Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 20:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ሀብቱ ለድቅድቅ ጨለማ ተዳርጓል፤ ሰው ባላራገበው እሳት ይበላል፤ በድንኳኑም ውስጥ የተረፈውን ይልሳል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ለከበሩ ዕቃዎቹ ጨለማ ተዘጋጅቶአል፥ በሰው እፍ ያልተባለች እሳት ትበላዋለች፥ በድንኳኑ ውስጥ የቀረውም ይጋያል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ያካበተው ንብረት ሁሉ ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ ውስጥ ይወድማል፤ በሰው እጅ ያልተቀጣጠለ እሳትም ያቃጥለዋል፤ በቤቱ ውስጥ የሚተርፈውን ንብረት ሁሉ ያጋየዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ጨለማ ሁሉ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል፤ ዕፍ የማ​ይ​ባል እሳ​ትም ይበ​ላ​ዋል፤ እን​ግ​ዳም ቤቱን ያጠ​ቃ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ጨለማ ሁሉ ስለ ከበረው ዕቃ ተዘጋጅቶአል፥ በሰው አፍ እፍ የማትባል እሳት ትበላዋለች፥ በድንኳኑ ውስጥ የቀረው ይጨነቅባታል።

参见章节 复制




ኢዮብ 20:26
13 交叉引用  

ከጨለማ አያመልጥም፤ ቅርንጫፎቹን ነበልባል ያደርቃቸዋል፤ በእግዚአብሔርም እስትንፋስ ይወሰዳል።


ቀኑ ጨለማ ይሆንባቸዋል፤ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳለ ሰው በዳበሳ ይሄዳሉ።


በተሳለ የጦረኛ ቀስት፣ በግራር ከሰል ፍም ይቀጣሃል።


በምትገለጥበት ጊዜ፣ እሳት እንደሚንቀለቀልበት ምድጃ ታደርጋቸዋለህ፤ እግዚአብሔር በመዓቱ እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋል፤ እሳቱም ሙጥጥ አድርጋ ትበላቸዋለች።


ከቀድሞ ጀምሮ ቶፌት የተባለ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅቷል፤ ለንጉሡም ተበጅቷል፤ ማንደጃ ጕድጓዱም ሰፊና ጥልቅ ነው፤ በውስጡም ብዙ እሳትና ማገዶ አለ፤ የእግዚአብሔርም እስትንፋስ እንደ ፈሳሽ ድኝ ያቀጣጥለዋል።


ከዚያም ወደ ምድር ይመለከታሉ፣ የሚያዩትም ጭንቀት፣ ጨለማና የሚያስፈራም ጭጋግ ብቻ ነው፤ ወደ ድቅድቅ ጨለማም ይጣላሉ።


መንሹ በእጁ ነው፤ ዐውድማውን ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውን በጐተራ ይከትታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


መንግሥተ ሰማይ ተዘጋጅቶላቸው የነበሩት ግን ወደ ውጭ ወደ ጨለማው ይጣላሉ። በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”


የነውራቸውን ዐረፋ የሚደፍቁ የተቈጡ የባሕር ማዕበል፣ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የሚጠብቃቸው ተንከራታች ከዋክብት ናቸው።


跟着我们:

广告


广告