Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 1:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እነሆ፤ ታላቅ ዐውሎ ነፋስ ከምድረ በዳ መጣ፤ የቤቱንም አራት ማእዘናት መታ፤ እርሱም በልጆቹ ላይ ወድቆ ገደላቸው። እኔም ብቻዬን አመለጥሁ፤ ልነግርህም መጣሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እነሆም፥ ብርቱ ነፋስ ከምድረበዳ መጥቶ የቤቱን አራቱን ማዕዘን መታው፥ በብላቴኖቹም ላይ ወደቀ፥ ሞቱም፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ከበረሓ የተነሣ ዐውሎ ነፋስ በድንገት መጥቶ ቤቱን በሙሉ በገለባበጠው ጊዜ ቤቱ በላያቸው ላይ ስለ ተደረመሰ ሞቱ፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እነሆ፥ ዐውሎ ነፋስ ከም​ድረ በዳ ድን​ገት መጥቶ ቤቱን በአ​ራት ማዕ​ዘኑ መታው፥ ቤቱም በብ​ላ​ቴ​ኖቹ ላይ ወደቀ፥ እነ​ር​ሱም ሞቱ፤ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እነሆም፥ ዐውሎ ነፋስ ከምድረ በዳ መጥቶ የቤቱን አራቱን ማዕዘን መታው፥ በብላቴኖቹም ላይ ወደቀ፥ ሞቱም፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ አለው።

参见章节 复制




ኢዮብ 1:19
12 交叉引用  

አባታቸው ያዕቆብም፣ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ ኧረ ምን ጕድ ነው የመጣብኝ!” አላቸው።


ንጉሡም እጅግ ዐዘነ፤ በቅጽር በሩ ዐናት ላይ ወዳለችው ቤት ወጥቶ አለቀሰ፤ ሲሄድም፣ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! በአንተ ፈንታ ምነው እኔ በሞትሁ ኖሮ! አቤሴሎም ሆይ፤ ልጄን! ወየው ልጄን!” ይል ነበር።


የቀሩት ወደ አፌቅ ከተማ ሸሹ፤ በዚያም በሃያ ሰባቱ ሺሕ ላይ ቅጥሩ ተንዶ ወደቀባቸው። ቤን ሃዳድም ወደ ከተማዪቱ ሸሽቶ በመሄድ ወደ አንዲት እልፍኝ ገብቶ ተደበቀ።


እርሱም እየተናገረ ሳለ፣ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ተሰብስበው እየበሉና እየጠጡ ሳሉ፣


ኢዮብም ተነሣ፤ ልብሱን ቀደደ፤ ራሱን ተላጨ፤ በምድርም ላይ ተደፍቶ ሰገደ፤


ዶፍ ወረደ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያን ቤት መታው፤ ቤቱም ወደቀ፤ አወዳደቁም የከፋ ነበር።”


የደሴቲቱ ነዋሪዎች እባብ በእጁ ላይ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ፣ “ይህ ሰው በርግጥ ነፍስ ገዳይ ነው፤ ከባሕር ቢያመልጥ እንኳ የፍርድ አምላክ በሕይወት እንዲኖር አልፈቀደለትም” ተባባሉ።


በዚህም፣ የዓለምን ክፉ መንገድ ተከትላችሁ፣ በአየር ላይ ላሉት መንፈሳውያን ኀይላት ገዥ ለሆነውና አሁንም ለእግዚአብሔር በማይታዘዙት ሰዎች ላይ ለሚሠራው መንፈስ እየታዘዛችሁ ትኖሩ ነበር።


“ከፍልስጥኤማውያን ጋራ አብሬ ልሙት” በማለት ባለ ኀይሉ ሲገፋው፣ ቤተ ጣዖቱ በገዦቹና በውስጡ በነበሩት በሌሎቹ ሰዎች ሁሉ ላይ ወደቀባቸው። ስለዚህ በሕይወት ከኖረበት ጊዜ ይልቅ በሞቱ ጊዜ ብዙ ሰው ገደለ።


跟着我们:

广告


广告