Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 7:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 “ይህን ሁሉ ትነግራቸዋለህ፤ እነርሱ ግን አይሰሙህም፤ ትጠራቸውማለህ፤ አይመልሱልህም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 “ይህን ሁሉ ቃላት ለእነርሱ ትናገራለህ፥ ነገር ግን አይሰሙህም፤ ትጠራቸዋለህ፥ ነገር ግን አይመልሱልህም።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 “እንዲሁም አንተ ኤርምያስ ሆይ! ይህን ሁሉ ቃል ለሕዝቤ ትነግራቸዋለህ፤ ነገር ግን አይሰሙህም፤ ትጠራቸዋለህ፤ አይመልሱልህም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 “ይህን ሁሉ ቃል ለዚህ ሕዝብ ትነ​ግ​ራ​ለህ፤ ነገር ግን አይ​ሰ​ሙ​ህም፤ ትጠ​ራ​ቸ​ው​ማ​ለህ፤ ነገር ግን አይ​መ​ል​ሱ​ል​ህም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 በዚህም ቃል ሁሉ ትነግራቸዋለህ፥ ነገር ግን አይሰሙህም፥ ትጠራቸውማለህ፥ ነገር ግን አይመልሱልህም።

参见章节 复制




ኤርምያስ 7:27
11 交叉引用  

በመጣሁ ጊዜ ለምን በዚያ ሰው አልነበረም? በተጣራሁስ ጊዜ የሚመልስ ሰው እንዴት በዚያ ታጣ? ስለ እናንተ ወጆ ለመክፈል ክንዴ ዐጥራ ነበርን? እናንተንስ ለማዳን ኀይል አነሰኝን? እነሆ፤ በተግሣጼ ባሕሩን አደርቃለሁ፤ ወንዞችን ምድረ በዳ አደርጋለሁ፤ ዓሦቻቸው ውሃ በማጣት ይሸታሉ፤ በጥማትም ይሞታሉ።


ተጣርቼ ስላልመለሳችሁ፣ ተናግሬ ስላልሰማችሁ፣ በፊቴ ክፉ ነገር ስላደረጋችሁ፣ የሚያስከፋኝን ነገር ስለ መረጣችሁ፣ ለሰይፍ እዳርጋችኋለሁ፤ ሁላችሁም ለመታረድ ትጐነበሳላችሁ።”


ይዋጉሃል፤ ዳሩ ግን አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አያሸንፉህም” ይላል እግዚአብሔር።


እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፤ “ ‘ገና ሕፃን ልጅ ነኝ’ አትበል፤ ወደምልክህ ሁሉ ሄደህ፣ ያዘዝሁህን ሁሉ ትናገራለህ፤


“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ቆመህ፣ ለማምለክ ወደ እግዚአብሔር ቤት ከይሁዳ ከተሞች ለሚመጣው ሕዝብ ሁሉ ተናገር፤ አንዲትም ቃል ሳታስቀር የማዝዝህን ሁሉ ንገራቸው።


“ ‘ስጠራቸው አልሰሙም፤ ስለዚህ ሲጠሩኝ አልሰማም’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሁሉ ለእናንተ ከመግለጽ የተቈጠብሁበት ጊዜ የለምና።


跟着我们:

广告


广告