Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 6:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 “ብረት እንደሚፈተን፣ የሕዝቤን መንገድ፣ አካሄዳቸውንም እንድትፈትን፣ አንተን ፈታኝ አድርጌሃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 “መንገዳቸውን እንድታውቅና እንድትፈትን በሕዝቤ መካከል አቅላጭና ፈታኝ አድርጌሃለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ኤርምያስ ሆይ! ብረት እንደሚፈተን ሕዝቤን ፈትነህ ምን ዐይነት እንደ ሆኑ ዕወቅ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 በተ​ፈ​ታኝ ሕዝቤ መካ​ከል ፈታኝ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንም በፈ​ተ​ንሁ ጊዜ ታው​ቀ​ኛ​ለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 መንገዳቸውን እንድታውቅና እንድትፈትን በሕዝቤ መካከል ፈታኝ አድርጌሃለሁ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 6:27
6 交叉引用  

እነሆ፤ ዛሬ በመላዪቱ ምድር ላይ አስነሣሃለሁ፤ ይኸውም የይሁዳን ነገሥታት፣ አለቆቿን፣ ካህናቷንና የምድሪቱን ሕዝብ ሁሉ መቋቋም እንድትችል የተመሸገ ከተማ፣ የብረት ምሰሶና የናስ ቅጥር አድርጌሃለሁ።


ለዚህ ሕዝብ የናስ ቅጥር፣ የተመሸገ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፤ ልታደግህና፣ ላድንህም፣ እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና፤ ቢዋጉህም እንኳ፣ ሊያሸንፉህ አይችሉም፤” ይላል እግዚአብሔር።


ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ እንደ ብረት አነጥራቸዋለሁ፤ እፈትናቸዋለሁም፤ ስለ ሕዝቤ ኀጢአት፣ ከዚህ የተለየ ምን ማድረግ እችላለሁ?


“የሰው ልጅ ሆይ፤ እነዚህን ለፍርድ ታቀርባቸዋለህን? በውኑ ለፍርድ ታቀርባቸዋለህን? የቀድሞ አባቶቻቸውን አስጸያፊ ተግባር ግለጥላቸው፤


“የሰው ልጅ ሆይ፤ አትፈርድባትምን? ደም በምታፈስሰው በዚህች ከተማ ላይ አትፈርድባትምን? ጸያፍ ተግባሯን ፊት ለፊት ንገራት፤


跟着我们:

广告


广告