Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 52:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ናቡከደነፆር በነገሠ በሃያ ሦስተኛው ዓመት፣ የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን፣ ሰባት መቶ አርባ ዐምስት አይሁድ ማርኮ ወስዷል። በአጠቃላይ አራት ሺሕ ስድስት መቶ ሰዎች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 በናቡከደነፆር በሀያ ሦስተኛው ዓመት የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ከአይሁድ ሰባት መቶ አርባ አምስት ሰው ማርኮ አፈለሰ፤ በአጠቃላይ የሰዎቹ ብዛት አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 እንዲሁም በነገሠ በሃያ ሦስት ዓመቱ ሰባት መቶ አርባ አምስት አይሁድ በናቡዛርዳን እጅ ተማርከው ተወስደዋል፤ በጠቅላላው ተማርከው የተወሰዱት ሰዎች ቊጥር አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በሃያ ሦስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የአ​ዛ​ዦቹ አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ከአ​ይ​ሁድ ሰባት መቶ አርባ አም​ስት ነፍስ ማር​ኮ​አል፤ ሰዎ​ችም ሁሉ አራት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 በናቡከደነፆር በሀያ ሦስተኛው ዓመት የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ከአይሁድ ሰባት መቶ አርባ አምስት ነፍስ ማርኮአል፥ ሰዎች ሁሉ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 52:30
6 交叉引用  

የክብር ዘቡ አዛዥ ናቡዘረዳን ድኾችንና በከተማዪቱ የቀረውን ሕዝብና ሸሽተው ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን አፈለሳቸው።


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በነገሠ በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት፣ በዐምስተኛው ወር ከወሩም በሰባተኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ባለሟል የክብር ዘበኞች አዛዥ የነበረው ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።


የባቢሎን መንግሥት የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን፣ በከተማዪቱ የቀረውን ሕዝብ ሁሉ ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው።


የክብር ዘቡ አዛዥ ናቡዘረዳን አንዳንድ የድኻ ድኾችንና በከተማዪቱ የቀረውን ሕዝብና ሸሽተው ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን ሰዎች ከእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ጋራ አፈለሳቸው።


ናቡከደነፆር በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት፣ ስምንት መቶ ሠላሳ ሁለት ሰዎች ከኢየሩሳሌም፤


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የወይን ፍሬ ተሟጦ እንደሚቃረም፣ ከእስራኤል የተረፉትን እንዲሁ ይቃርሟቸው። ወይን ለቃሚ እንደሚለቅም፣ እጅህን ወደ ቅርንጫፎቹ ደጋግመህ ዘርጋ።”


跟着我们:

广告


广告