ኤርምያስ 51:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ከአንቺ ለማእዘን የሚሆን ድንጋይ፣ ለመሠረትም የሚሆን ዐለት አይወሰድም፤ ለዘላለም ባድማ ትሆኛለሽ፤” ይላል እግዚአብሔር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ከአንተም ለማዕዘንና ለመሠረት የሚሆን ድንጋይ አይወስዱም፥ ለዘለዓለምም ባድማ ትሆናለህ፥ ይላል ጌታ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 ለማእዘን ወይም ለመሠረት የሚያገለግል ድንጋይ አይገኝብሽም፥ አንቺ ለዘለዓለሙ ምድረ በዳ ትሆኚአለሽ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ከአንተም ለማዕዘን የሚሆን ድንጋይንና ለመሠረት የሚሆን ድንጋይን አይወስዱም፤ ለዘለዓለምም አጠፋሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ከአንተም ለማዕዘንና ለመሠረት የሚሆን ድንጋይ አይወስዱም፥ ለዘላለምም ባድማ ትሆናለህ፥ ይላል እግዚአብሔር። 参见章节 |