ኤርምያስ 49:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ስለዚህ በአሞናውያን ከተማ በረባት ላይ፣ የጦርነት ውካታ ድምፅ የሚሰማበት ጊዜ ይመጣል፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “እርሷም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፤ በዙሪያዋ ያሉት መንደሮችም ይቃጠላሉ፤ እስራኤልም ከአገሯ ያስወጧትን፣ ከአገሯ ታስወጣለች፤” ይላል እግዚአብሔር፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአሞን ልጆች ከተማ በረባት ላይ የጦርነት ውካታን የማሰማበት ቀኖች ይመጣሉ፥ ይላል ጌታ፤ የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች፥ ሴቶች ልጆችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፥ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል ጌታ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ስለዚህ የአሞን ከተማ በሆነችው በራባ ላይ የጦርነት ክተት ጥሪ ድምፅ የማሰማበት ጊዜ ይመጣል፤ እርስዋ፥ በፍርስራሽ ክምር የተሞላች ባድማ ትሆናለች፤ መንደሮችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፤ ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን አስቀድመው እነርሱን የበዘበዙአቸውን መልሰው ይበዘብዛሉ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ስለዚህ እነሆ በአሞን ልጆች ከተማ በራባት ላይ የሰልፍ ውካታን የማሰማበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ለጥፋትም ትሆናለች፥ መንደሮችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፤ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል እግዚአብሔር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአሞን ልጆች ከተማ በረባት ላይ የሰልፍ ውካታን የማሰማበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች፥ ሴቶች ልጆችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፥ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል እግዚአብሔር። 参见章节 |