Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 48:39 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 “እንዴት ተንኰታኰተ! ምንኛስ አለቀሱ! ሞዓብ እንዴት ዐፍሮ ጀርባውን አዞረ! ሞዓብ የመሰደቢያ፣ በዙሪያው ላሉትም ሁሉ የሽብር ምልክት ሆነ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 እንዴት ተሰበረ! እንዴትስ አለቀሱ! በእፍረትም የተነሣ ሞዓብ ጀርባውን እንዴት ሰጠ! ስለዚህ ሞዓብ በዙሪያው ላሉት ሁሉ መሳቂያና መደንገጫ ሆኖአል።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 በሞአብ ላይ ምን ዐይነት አስደንጋጭ ሁናቴ ደርሶ ነው የምታለቅሰው? እንዴትስ በዕፍረት ጀርባዋን ትሰጣለች? ስለዚህም ለጐረቤቶችዋ ሁሉ መሳለቂያና አስደንጋጭ ሆናለች።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 እን​ዴት ተለ​ወ​ጠች! ከእ​ፍ​ረ​ትም የተ​ነሣ ሞአብ ጀር​ባ​ዋን እን​ዴት መለ​ሰች! ሞአ​ብም በዙ​ሪ​ያዋ ላሉት ሁሉ መሳ​ቂ​ያና መሳ​ለ​ቂያ ትሆ​ና​ለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 እንዴት ተገለበጠ! በእፍረትም የተነሣ ሞዓብ ጀርባውን እንዴት መለሰ! ብላችሁ አልቅሱ። ሞዓብም በዙሪያው ላሉት ሁሉ መሳቂያና ድንጋጤ ይሆናል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 48:39
10 交叉引用  

የእስራኤል ቤት፤ በቤቴል ታምኖ እንዳፈረ ሁሉ፣ ሞዓብም በካሞሽ ያፍራል።


በዙሪያው የምትኖሩ ሁሉ፤ ዝናውን የምታውቁ ሁሉ አልቅሱለት፤ ‘ብርቱው ከዘራ፣ የከበረው በትር እንዴት ሊሰበር ቻለ’ በሉ።


በሕዝብ ተሞልታ የነበረችው ከተማ፣ እንዴት የተተወች ሆና ቀረች! በሕዝቦች መካከል ታላቅ የነበረችው፣ እርሷ እንዴት እንደ መበለት ሆነች! በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው፣ አሁን ባሪያ ሆናለች።


ጌታ የጽዮንን ሴት ልጅ፣ በቍጣው ደመና እንዴት ጋረዳት! ከሰማይ ወደ ምድር፣ የእስራኤልን ክብር ወርውሮ ጣለው፤ በቍጣው ቀን፣ የእግሩን መቀመጫ አላስታወሰም።


ወርቁ እንዴት ደበሰ! ንጹሑስ ወርቅ እንዴት ተለወጠ! የከበሩ ድንጋዮች፣ በየመንገዱ ዳር ተበታትነዋል።


跟着我们:

广告


广告