ኤርምያስ 48:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም17 በዙሪያው የምትኖሩ ሁሉ፤ ዝናውን የምታውቁ ሁሉ አልቅሱለት፤ ‘ብርቱው ከዘራ፣ የከበረው በትር እንዴት ሊሰበር ቻለ’ በሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 በዙሪያው ያላችሁ ሁሉ ስሙንም የምታውቁ ሁሉ፦ ብርቱው በትረ መንግሥት፥ የከበረው ሽመል፥ እንዴት ተሰበረ!፥ ብላችሁ አልቅሱለት። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 “ዝናዋን የምታውቁና በአቅራቢያዋ የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ‘የሥልጣን ምልክት የሆነው የተከበረው ኀይልዋ፥ በትረ መንግሥትዋ እንዴት ተሰበረ’ በማለት ዋይ! ብላችሁ አልቅሱላት! 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 በዙሪያው ያላችሁ ሁሉ ስሙንም የምታውቁ ሁሉ፦ ታላቁ በትር፥ ጠንካራውም ሽመል፥ እንዴት ተሰበረ! ብላችሁ አልቅሱለት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 በዙሪያው ያላችሁ ሁሉ ስሙንም የምታውቁ ሁሉ፦ ብርቱው በትር፥ የከበረው ሽመል፥ እንዴት ተሰበረ! ብላችሁ አልቅሱለት። 参见章节 |