Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 46:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ጠላት ገፍቶ ሲመጣባት፣ ግብጽ እንደሚሸሽ እባብ ታፏጫለች፤ ዛፍ እንደሚቈርጡ ሰዎች፣ መጥረቢያ ይዘው ይመጡባታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 “ጠላቶችዋ በኃይል ዘምተው እንደ እንጨት ቈራጮች በምሳር ይመጡባታልና በደረቱ እንደሚሽሎኮሎክ እባብ ድምፅ ታሰማለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22-23 የጠላት ሠራዊት ኀይል ሲቃረብ ግብጽ እንደ እባብ የፉጨት ድምፅ እያሰማች ትሸሻለች፤ ሰዎች ጥቅጥቅ ያለውን ደን እንደሚመነጥሩ በመጥረቢያ አደጋ ይጥሉባታል። የሰዎቻቸው ብዛት በቊጥር አይደረስበትም፤ የወታደሮቻቸውም ብዛት ከአንበጣ ሠራዊት ይበልጣል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሠራ​ዊ​ትም በኀ​ይል ይዘ​ም​ቱ​ባ​ታ​ልና፥ እንደ እን​ጨት ቈራ​ጮ​ችም በም​ሳር ይመ​ጡ​ባ​ታ​ልና ድም​ፅዋ እን​ደ​ም​ት​ሸሽ እባብ ይተ​ማል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ከሠራዊትም ጋር ይሄዳሉና ድምፅ እንደ እባብ ይተምማል፥ እንደ እንጨት ቈራጮችም በምሳር ይመጡባታል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 46:22
13 交叉引用  

በጫካ መካከል ዛፎችን ለመቍረጥ፣ መጥረቢያ የሚያነሣ ሰው መሰሉ።


መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይኵራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፣ ዘንግም ራሱን ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኵራራ ነው።


ጥድና የሊባኖስ ዝግባ እንኳ ደስ ብሏቸው፣ “አንተም ወደቅህ፤ ዕንጨት ቈራጭም መጥረቢያ አላነሣብንም” አሉ።


ወደ ታች ትወርጃለሽ፤ ከምድርም በታች ትናገሪያለሽ፤ ንግግርሽ ከትቢያ እየተጕተመተመ ይወጣል፤ ድምፅሽ እንደ መናፍስት ድምፅ ከመሬት ወደ ላይ ይመጣል፤ ንግግርሽ ከትቢያ ያንሾካሹካል።


በመልእክተኞችህ በኩል፣ በጌታ ላይ ብዙ የስድብ ቃል ተናገርህ፤ እንዲህም አልህ፤ ‘በሠረገሎቼ ብዛት፣ የተራሮችንም ከፍታ፣ የሊባኖስንም ጫፍ ወጥቻለሁ፤ ረዣዥም ዝግባዎችን፣ የተመረጡ ጥዶችን ቈርጫለሁ፤ እጅግ ወደራቁት ከፍታዎች፣ እጅግ ውብ ወደሆኑትም ደኖች ደርሻለሁ፤


ቅጥረኞች ወታደሮቿም እንደ ሠቡ ወይፈኖች ናቸው፤ የሚቀጡበት ጊዜ ስለ ደረሰ፣ ጥፋታቸው ስለ ተቃረበ፣ እነርሱም ወደ ኋላ ተመልሰው በአንድነት ይሸሻሉ፤ በቦታቸውም ጸንተው ሊቋቋሙ አይችሉም።


ጥቅጥቅ ጫካ ቢሆንም፣ ደኗን ይመነጥራሉ፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “ብዛታቸው እንደ አንበጣ ነው፤ ሊቈጠሩም አይችሉም።


በዚህ ምክንያት አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይም እላለሁ፤ ባዶ እግሬንና ዕርቃኔን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ፤ እንደ ጕጕትም አቃስታለሁ።


አሕዛብ ያያሉ፣ ያፍራሉም፤ ኀይላቸውን ሁሉ ያጣሉ፤ አፋቸውን በእጃቸው ይይዛሉ፤ ጆሯቸውም ትደነቍራለች።


የጥድ ዛፍ ሆይ፤ ዝግባ ወድቋልና አልቅስ፤ የከበሩትም ዛፎች ጠፍተዋል! የባሳን ወርካዎች ሆይ፤ አልቅሱ፤ ጥቅጥቅ ያለው ደን ተመንጥሯል!


ነገር ግን ለማኅበረ ሰቡ በሙሉ ዕንጨት እየቈረጡ ውሃ እየቀዱ ይኑሩ።” ስለዚህ መሪዎቹ የገቡላቸው ቃል ተጠበቀ።


跟着我们:

广告


广告