Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 46:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 በዚያም የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን፣ ‘በተሰጠው ዕድል ያልተጠቀመ፣ አለሁ አለሁ ባይ ደንፊ!’ ብለው ይጠሩታል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በዚያም የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንን፦ ሰዓቱን የሚያሳልፍ ለፍላፊ ብለው ጠሩት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የግብጽን ንጉሥ “በዕድሉ የማይጠቀም ለፍላፊ፥” በሚል አዲስ ስም ይጠሩታል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በዚ​ያም የግ​ብፅ ንጉሥ የፈ​ር​ዖ​ንን ስም ጊዜ​ውን የሚ​ያ​ሳ​ልፍ ብለው ጠሩት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በዚያም የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንን፦ ሰዓቱን የሚያሳልፍ ጕረኛ ብለው ጠሩት።

参见章节 复制




ኤርምያስ 46:17
11 交叉引用  

ከዚያም ቤን ሃዳድ፣ “ለሚከተለኝ ሰው ሁሉ የሰማርያ ዐፈር አንዳንድ ዕፍኝ የሚዳረስ ሳይሆን ቢቀር፣ አማልክት ይህን ያድርጉብኝ፤ ከዚህ የባሰም ያምጡብኝ” ሲል ሌሎች መልክተኞችን ወደ አክዓብ ላከ።


የእስራኤልም ንጉሥ፣ “ ‘ታጥቆ ለጦርነት የሚወጣ ሰው የጦር ትጥቁን እንደ ፈታ ሰው መደንፋት የለበትም’ ብላችሁ ንገሩት” አላቸው።


እርሱም፣ “አመጣጣቸው ለሰላምም ይሁን ለጦርነት ከነሕይወታቸው ይዛችሁ አምጧቸው” አለ።


አንተ ግን እስትንፋስህን አነፈስህ፤ ባሕርም ከደናቸው፤ በኀያላን ውሆች፣ እንደ ብረት ሰጠሙ።


ጠላት፣ ‘አሳድዳቸዋለሁ፤ እማርካቸዋለሁ፤ ምርኮን እካፈላለሁ፤ ነፍሴ በእነርሱ ትጠግባለች፤ ሰይፌን እመዝዛለሁ፤ እጄም ትደመስሳቸዋለች አለ።’


ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው፤


ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ እግዚአብሔር እጁን ሲዘረጋ፣ ርዳታ ሰጪው ይሰናከላል፤ ተረጂውም ይወድቃል፤ ሁለቱም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።


እንዲህም ብለህ ተናገረው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። “ ‘በወንዞችህ መካከል የምትተኛ አንተ ታላቅ አውሬ፣ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን፤ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ። “የአባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ ለራሴም ሠርቼዋለሁ” ትላለህ።


“ ‘በዔድን ካሉት ዛፎች በውበትና በትልቅነት የሚወዳደርህ የትኛው ነው? ይሁን እንጂ አንተም እንደዚሁ ከዔድን ዛፎች ጋራ ከመሬት በታች ትወርዳለህ፤ በሰይፍ ከተገደሉት፣ ካልተገረዙትም መካከል ትጋደማለህ። “ ‘እንግዲህ ፈርዖንና ስፍር ቍጥር የሌለው ሕዝቡ የሚደርስባቸው ይህ ነው፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”


跟着我们:

广告


广告