Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 44:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ኤርምያስም ለሕዝቡና ለሴቶቹ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “በግብጽ የምትኖሩ የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ ለሴቶቹም ሁሉ እንዲህ አለ፦ “በግብጽ ምድር የምትገኙ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ስሙ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24-25 ከይሁዳ ተሰደው በግብጽ ስለሚኖሩት ሕዝብ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ የነገረኝን ሁሉ ለሕዝቡ ሁሉ በተለይም ለሴቶቹ እንዲህ በማለት ነገርኳቸው፦ “እናንተና ሚስቶቻችሁ ለሰማይ ንግሥት ስእለት ለመስጠት ቃል ገብታችኋል፤ ይኸውም እናንተ ለእርስዋ ዕጣን ልታጥኑላት፥ የወይን ጠጅም መባ ልታፈሱላት የገባችሁትን ቃል ኪዳን ፈጽማችኋል፤ እንግዲያውስ ቀጥሉ፤ የገባችሁትን ቃል ጠብቁ፤ መሐላችሁንም ፈጽሙ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ኤር​ም​ያ​ስም ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ ለሴ​ቶ​ቹም ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “በግ​ብፅ ምድር የም​ት​ኖሩ አይ​ሁድ ሁሉ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ ለሴቶቹም ሁሉ እንዲህ አለ፦ በግብጽ ምድር የምትኖሩ ይሁዳ ሁሉ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 44:24
11 交叉引用  

ከዚያም ሚክያስ እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፣ የሰማይም ሰራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።


እናንተ የሰዶም ገዦች፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እናንተ የገሞራ ሰዎች፤ የአምላካችንን ሕግ አድምጡ።


ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለውን ሕዝብ የምትገዙ፣ እናንተ ፌዘኞች የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።


እንግዲህ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ወደ ግብጽ ለመሄድ ወስናችሁ እዚያ ለመቀመጥ ብትሄዱ፣


የእግዚአብሔርንም ቃል ባለመታዘዝ ወደ ግብጽ ገቡ፤ ዘልቀውም እስከ ጣፍናስ ድረስ ሄዱ።


በግብጽ የምትኖሩ አይሁድ ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ከእንግዲህ ወዲህ በየትኛውም የግብጽ ክፍል የሚኖር ማንኛውም አይሁዳዊ፣ “ሕያው እግዚአብሔርን!” ብሎ ስሜን እንዳይጠራ፣ እንዳይምልም በታላቁ ስሜ ምያለሁ፤


እነርሱ ዐመፀኛ ቤት ስለ ሆኑ፣ ቢሰሙም ባይሰሙም አንተ ቃሌን ንገራቸው።


እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ። “አንተ፣ ‘በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፤ በይሥሐቅም ቤት ላይ አትስበክ’ ትላለህ።


ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ።


跟着我们:

广告


广告