Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 35:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ‘የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ልጆቹ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ አዘዛቸው፤ ይህም ትእዛዝ ተጠብቋል፤ የአባታቸውን ትእዛዝ ስለ ጠበቁ እስከ ዛሬ ድረስ የወይን ጠጅ አይጠጡም፤ እናንተ ግን እኔ ደጋግሜ ብናገራችሁም፤ አልታዘዛችሁኝም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ልጆቹን የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ ያዘዛቸው ቃላት ተፈጸሙ፤ ለአባታቸውም ትእዛዝ ታዝዘዋልና እስከ ዛሬ ድረስ አይጠጡም፤ እኔም በማለዳ ተነሥቼ ተናገርኋቸው፤ ተናገርሁ፥ ሆኖም ግን አልሰማችሁኝም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የኢዮናዳብ ዘሮች እንኳ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ አባታቸው ያዘዛቸውን ቃል በመጠበቅ እነሆ እስከ አሁን ድረስ ምንም ዐይነት የወይን ጠጅ አይቀምሱም፤ እኔ ግን ሁልጊዜ በመደጋገም እነግራችኋለሁ፤ እናንተ ልትታዘዙኝ አልፈለጋችሁም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የሬ​ካብ ልጅ ኢዮ​ና​ዳብ ልጆቹ የወ​ይን ጠጅ እን​ዳ​ይ​ጠጡ ያዘ​ዛ​ቸው ቃል ተፈ​ጸመ፤ ለአ​ባ​ታ​ቸ​ውም ትእ​ዛዝ ታዝ​ዘ​ዋ​ልና እስከ ዛሬ ድረስ ወይን አይ​ጠ​ጡም፤ እኔም በማ​ለዳ ስለ እና​ንተ ተና​ገ​ርሁ፤ ሆኖም አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ልጆቹ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ ያዘዛቸው ቃል ተፈጸመ፥ ለአባታቸውም ትእዛዝ ታዝዘዋልና እስከ ዛሬ ድረስ አይጠጡም፥ እኔም በማለዳ ተነሥቼ ተናግሬአችኋለሁ፥ ተናገርሁ፥ ሆኖም አልሰማችሁኝም።

参见章节 复制




ኤርምያስ 35:14
15 交叉引用  

“ነገር ግን እንቢተኞች ሆኑ፤ ዐመፁብህም፤ ሕግህንም አሽቀንጥረው ጣሉ፤ ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩት ነቢያትህን ገደሉ፤ አስጸያፊ የስድብ ቃልም ተናገሩ።


ብዙ ዘመን ታገሥሃቸው፤ በነቢያትህ አማካይነት በመንፈስህ አስጠነቀቅሃቸው። ነገር ግን አላደመጡህም፤ ከዚህም የተነሣ ጎረቤቶቻቸው ለሆኑ አሕዛብ አሳልፈህ ሰጠሃቸው።


እነዚህም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለመስማት የማይፈልጉ፣ ዐመፀኛ ሕዝቦችና አታላይ ልጆች ናቸው።


በመጣሁ ጊዜ ለምን በዚያ ሰው አልነበረም? በተጣራሁስ ጊዜ የሚመልስ ሰው እንዴት በዚያ ታጣ? ስለ እናንተ ወጆ ለመክፈል ክንዴ ዐጥራ ነበርን? እናንተንስ ለማዳን ኀይል አነሰኝን? እነሆ፤ በተግሣጼ ባሕሩን አደርቃለሁ፤ ወንዞችን ምድረ በዳ አደርጋለሁ፤ ዓሦቻቸው ውሃ በማጣት ይሸታሉ፤ በጥማትም ይሞታሉ።


የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ “ታዘዙኝ” በማለት ደጋግሜ አስጠነቀቅኋቸው።


ልትሰሟቸው ይገባ የነበረውን ወደ እናንተ ደጋግሜ የላክኋቸውን የአገልጋዮቼን የነቢያትን ቃል ባትሰሙ፣


በአገልጋዮቼ በነቢያት በኩል ደጋግሜ የላክሁላቸውን ቃሌን አልሰሙምና” ይላል እግዚአብሔር፤ “እናንተ ምርኮኞችም አልሰማችሁም” ይላል እግዚአብሔር።


ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ፤ ደጋግሜ ባስተምራቸውም አይሰሙም፤ ተግሣጽም አይቀበሉም።


የሬካብ ልጅ የኢዮናዳብ ዘሮች አባታቸው የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠብቀዋል፤ ይህ ሕዝብ ግን አልታዘዘኝም።’


እነርሱ ግን እንዲህ አሉ፤ “የወይን ጠጅ አንጠጣም፤ አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ እንዲህ ብሎ አዝዞናል፤ ‘እናንተና ዘራችሁ ከቶ የወይን ጠጅ አትጠጡ፤


እነዚህን ሁሉ ስታደርጉ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ደጋግሜ ተናገርኋችሁ፤ እናንተ ግን አላደመጣችሁኝም፤ ጠራኋችሁ፤ እናንተ ግን አልመለሳችሁም።


跟着我们:

广告


广告