Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 33:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በተራራማው አገር፣ በምዕራብ ተራሮች ግርጌና በኔጌብ ባሉ ከተሞች በብንያም አገር፣ በይሁዳ ከተሞች እንዲሁም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ መንደሮች መንጎች እንደ ገና በሚቈጥራቸው ሰው እጅ ሥር ያልፋሉ’ ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች፥ በቈላውም ባሉ ከተሞች፥ በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም አገር፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች በጎቹ መንጋውን በሚቆጥረው ሰው እጅ ሥር እንደገና ያልፋሉ፥ ይላል ጌታ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በተራራማው አገር በኮረብቶች ግርጌና በይሁዳ ደቡብ ባሉ ከተሞች፥ በብንያም ክፍለ ግዛት፥ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉት መንደሮችና በይሁዳ የገጠር ከተሞች ሁሉ እረኞች እንደገና በጎቻቸውን ይቈጥራሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በደ​ጋው ላይ ባሉ ከተ​ሞች፥ በቆ​ላ​ውም ባሉ ከተ​ሞች፥ በደ​ቡ​ብም ባሉ ከተ​ሞች፥ በብ​ን​ያ​ምም ሀገር፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዙሪያ ባሉ ስፍ​ራ​ዎች፥ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች በጎቹ በተ​ቈ​ጣ​ጣ​ሪ​ያ​ቸው እጅ እንደ ገና ያል​ፋሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች በቈላውም ባሉ ከተሞች በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም አገር በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች መንጎቹ በተቈጣጣሪው እጅ እንደ ገና ያልፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ኤርምያስ 33:13
9 交叉引用  

ሰዎች ከይሁዳ ከተሞች፣ ከኢየሩሳሌም ዙሪያ፣ ከብንያምም አገር፣ ከቈላውና ከደጋው አገር እንዲሁም ከኔጌብ የሚቃጠል መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባን፣ ዕጣንና የምስጋና መሥዋዕት ይዘው ወደ እግዚአብሔር ቤት ይመጣሉ።


መጥተውም በጽዮን ተራራ ላይ በደስታ ይዘምራሉ፤ በእግዚአብሔርም ልግስና፣ በእህሉ፣ በወይን ጭማቂውና በዘይቱ፣ በፍየልና በበግ ጠቦት፣ በወይፈንና በጊደር ደስ ይሰኛሉ፤ ውሃ እንደማይቋረጥባት የአትክልት ስፍራ ይሆናሉ፤ ከእንግዲህም አያዝኑም።


የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ሰዎች በዚህ ምድር ቤት፣ የዕርሻ ቦታና የወይን አትክልት ስፍራ እንደ ገና ይገዛሉ።’


ምርኳቸውን ስለምመልስላቸው በብንያም አገር፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ መንደሮች፣ በይሁዳ ከተሞችና በተራራማው አገር ከተሞች፣ በምዕራብ ተራሮች ግርጌና በኔጌብ ባሉ ከተሞች፣ መሬት በጥሬ ብር ይገዛል፤ ውሉም ተፈርሞ፤ በምስክሮች ፊት ይታሸጋል፤’ ይላል እግዚአብሔር።”


ከበትሬ በታች አሳልፋችኋለሁ፤ ከቃል ኪዳኔም ጋራ አጣብቃችኋለሁ።


ከቀንድ ከብቶች፣ ከበጎችና ከፍየሎች መንጋ የሚወጣው ዐሥራት ከእረኛ በትር በታች ከሚያልፉት ዐሥረኛው እንስሳ ይሆናል፤ ይህም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።


በከነዓን ያለው ይህ የእስራኤል ስደተኞች ወገን፣ እስከ ሰራፕታ ያለውን ምድር ይወርሳል፤ በሰፋራድም ያሉ የኢየሩሳሌም ስደተኞች፣ የኔጌብን ከተሞች ይወርሳሉ።


“ከእናንተ መካከል አንዱ መቶ በጎች ቢኖሩትና ከእነርሱ አንዱ ቢጠፋበት፣ ዘጠና ዘጠኙን በሜዳ ላይ ጥሎ የጠፋውን እስኪያገኝ ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ማን ነው?


跟着我们:

广告


广告