Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 31:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ነገር ግን፣ እያንዳንዱ በገዛ ኀጢአቱ ይሞታል፤ ጐምዛዛ የወይን ፍሬ የሚበላ ሰው ሁሉ የራሱን ጥርስ ይጠርሳል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ነገር ግን ሰው ሁሉ በገዛ በደሉ ይሞታል፤ መራራውን የወይን ፍሬ የሚበላ ሁሉ ጥርሶቹ የተጠረሱ ይሆናሉ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ይህ መሆኑ ቀርቶ ጎምዛዛ የወይን ፍሬ የሚበላ ሰው ሁሉ የገዛ ራሱን ጥርስ ብቻ ያጠርሳል፤ እያንዳንዱም በገዛ ራሱ ኃጢአት ይሞታል።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ነገር ግን ሰው ሁሉ በገዛ በደሉ ይሞ​ታል፤ ጮር​ቃ​ውን የወ​ይን ፍሬ የሚ​በ​ላም ሁሉ ጥር​ሶቹ ይጠ​ር​ሳሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ነገር ግን ሰው ሁሉ በገዛ በደሉ ይሞታል፥ መራራውን የወይን ፍሬ የሚበላ ሁሉ ጥርሶቹ ይጠርሳሉ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 31:30
14 交叉引用  

ይሁን እንጂ በሙሴ የሕግ መጽሐፍ እግዚአብሔር፣ “ሰው ሁሉ በገዛ ኀጢአቱ ይሙት እንጂ ወላጆች በልጆቻቸው አይገደሉ፣ ልጆችም በወላጆቻቸው ኀጢአት አይገደሉ” ሲል ያዘዘ በመሆኑ፣ የነፍሰ ገዳዩን ልጆች አልገደላቸውም።


ዐይኖቹ የራሱን ውድቀት ይዩ፤ ከሁሉን ቻይ አምላክ ቍጣ ይጠጣ።


በደለኞች ወዮላቸው! ጥፋት ይመጣባቸዋል! የእጃቸውን ያገኛሉና።


መሞት የሚገባት ኀጢአት የሠራችው ነፍስ ናት። ልጅ በአባቱ ኀጢአት አይቀጣም፤ አባትም በልጁ ኀጢአት አይቀጣም። ጻድቁ የጽድቁን ፍሬ ያገኛል፤ ኀጢአተኛውም የኀጢአቱን ዋጋ ይቀበላል።


እነሆ ነፍስ ሁሉ የእኔ ናት፤ የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች ሁሉ የልጁም ነፍስ የእኔ ናት፤ ኀጢአት የምትሠራ ነፍስ እርሷ ትሞታለች።


መንፈስ በውስጤ ገብቶ በእግሬ አቆመኝ፤ እንዲህም ሲል ተናገረኝ፤ “ሂድ፤ ቤትህ ገብተህ በርህን ዝጋ።


ጻድቁን ሰው በርግጥ በሕይወት ትኖራለህ ብለው፣ እርሱም ጽድቁን ተማምኖ ክፋት ቢሠራ፣ ከሠራው ጽድቅ አንዱም አይታሰብለትም፤ በኀጢአቱም ምክንያት ይሞታል።


ጻድቅ ከጽድቁ ተመልሶ ክፉ ቢሠራ፣ ይሞትበታል።


ኀጢአተኛውን፣ ‘አንተ ክፉ ሰው፤ በርግጥ ትሞታለህ’ ባልሁት ጊዜ፣ ከመንገዱ እንዲመለስ ባታደርገው፣ ያ ክፉ ሰው በኀጢአቱ ይሞታል፤ አንተን ግን ስለ ደሙ እጠይቅሃለሁ።


እያንዳንዱ የራሱን ሸክም ሊሸከም ይገባዋልና።


አባቶች በልጆቻቸው፣ ልጆችም በአባቶቻቸው አይገደሉ፤ እያንዳንዱ በራሱ ኀጢአት ይገደል።


ምኞትም ከፀነሰች በኋላ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።


跟着我们:

广告


广告