Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 30:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እስኪ ጠይቁ፤ ተመልከቱም፤ ወንድ መውለድ ይችላል? ታዲያ ወንድ ሁሉ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ እጁን በሆዱ ላይ አድርጎ፣ የሰውስ ሁሉ ፊት ጠቍሮ የማየው ለምንድን ነው?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ጠይቁ፥ ወንድ ይወልድ እንደሆነ ተመልከቱ፤ ስለምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ ሴት እጁን በወገቡ ላይ አድርጎ ፊቱም ሁሉ ገርጥቶ አየሁ?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እስቲ ቆም ብላችሁ አስቡ! ወንድ አምጦ ልጅን መውለድ ይችላልን? ታዲያ ወንድ ሁሉ እንደ ወላድ ሴት በእጆቹ ወገቡን ይዞ የማየው ስለምንድን ነው? የእያንዳንዱስ ሰው ፊት ስለምን ገረጣ?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ጠይቁ፤ ወንድ ይወ​ልድ እንደ ሆነ ተመ​ል​ከቱ፤ ስለ ምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ እጁን በወ​ገቡ ላይ አድ​ርጎ፥ ፊቱም ሁሉ ወደ ጥቍ​ረት ተለ​ውጦ አየሁ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ጠይቁ፥ ወንድ ይወልድ እንደ ሆነ ተመልከቱ፥ ስለ ምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ እጁን በወገቡ ላይ አድርጎ ፊቱም ሁሉ ወደ ጥቁረት ተለውጦ አየሁ?

参见章节 复制




ኤርምያስ 30:6
19 交叉引用  

ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ በዚያ ብርክ ያዛቸው።


ወገቤ በዚህ ሥቃይ ተሞላ፤ በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ጭንቅ ያዘኝ፤ በሰማሁት ነገር ተንገዳገድሁ፤ ባየሁትም ነገር ተሸበርሁ።


ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠው እግዚአብሔር ለያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፤ “ያዕቆብ ከእንግዲህ ወዲያ አያፍርም፤ ፊቱም ከእንግዲህ አይለዋወጥም።


ልዩ ወዳጆች እንዲሆኑሽ ያስተማርሻቸው፣ ባለሥልጣን ሲሆኑብሽ ምን ትያለሽ? እንደምትወልድ ሴት፣ ምጥ አይዝሽምን?


አንቺ፣ ‘በሊባኖስ’ ውስጥ የምትኖሪ፣ መኖሪያሽን በዝግባ ዛፍ የሠራሽ ሆይ፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ መከራ በላይሽ ሲመጣ ጩኸትሽ እንዴት ይሆን!


የበኵር ልጇን ለመውለድ እንደምታምጥ፣ በወሊድ እንደምትጨነቅ ሴት ድምፅ ሰማሁ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ትንፋሽ ዐጥሯት ስትጮኽ፣ እጇን ዘርግታ፣ “ወዮልኝ! ተዝለፈለፍሁ፣ በነፍሰ ገዳዮች እጅ ወደቅሁ!” ስትል ሰማሁ።


ከተሞቹ ይወረራሉ፤ ምሽጎቹም ይያዛሉ፤ በዚያ ቀን የሞዓብ ጦረኞች ልብ፣ በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ልብ ይሆናል።


እነሆ፤ እንደ ንስር ተወርውሮ ይወርድባታል፤ ክንፎቹንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፤ በዚያ ቀን የኤዶም ጦረኞች ልብ፣ በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ልብ ይሆናል።


ደማስቆ ተዳከመች፤ ትሸሽም ዘንድ ወደ ኋላ ተመለሰች፤ ብርክ ያዛት፣ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ ጭንቅና መከራ ዋጣት።


የባቢሎን ንጉሥ ስለ እነርሱ ሰማ፤ እጆቹም በድን ሆኑ፤ ጭንቀት ይዞታል፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ታምሟል።


ስለ እነርሱ ወሬ ደርሶናል፤ ክንዶቻችንም ዝለዋል፤ ጭንቀት ይዞናል፤ እንደምታምጥም ሴት ሆነናል።


በዚያ ጊዜ ንጉሡ በድንጋጤ ተሞላ፤ ፊቱም ተለዋወጠ፤ እጆቹና እግሮቹ ከዱት፤ ጕልበቶቹም ተብረከረኩ።


በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ጭንቅ ይመጣበታል፤ እርሱ ግን ጥበብ የሌለው ልጅ ነው፤ የሚወለድበት ጊዜ ሲደርስ፣ ከእናቱ ማሕፀን መውጣት የማይፈልግ ሕፃን ነው።


በእነርሱ ፊት ሕዝቦች ይርዳሉ፤ የሁሉም ፊት ይገረጣል።


ተበዝብዛለች፤ ተዘርፋለች፤ ተራቍታለች። ልብ ቀልጧል፤ ጕልበት ተብረክርኳል፤ ሰውነት ተንቀጥቅጧል፤ ፊት ሁሉ ገርጥቷል።


ሰዎች፣ “ሰላምና ደኅንነት ነው” ሲሉ፣ ምጥ እርጉዝ ሴትን እንደሚይዛት እንዲሁ ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።


跟着我们:

广告


广告