Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 28:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ነቢዩ ኤርምያስም ለነቢዩ ሐናንያ እንዲህ አለው፤ “ሐናንያ ሆይ፤ ስማ! እግዚአብሔር ሳይልክህ ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ነቢዩም ኤርምያስ ነቢዩን ሐናንያን፦ “ሐናንያ ሆይ! ስማ፤ ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል እንጂ ጌታ አልላከህም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እኔም ይህንኑ ለሐናንያ እንዲህ ብዬ ነገርኩት፦ “ሐናንያ ሆይ! ስማ፤ አንተን እኮ እግዚአብሔር አላከህም፤ ይህንንም ሁሉ ሕዝብ ሐሰት በሆነ ነገር እንዲተማመን አድርገሃል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ነቢ​ዩም ኤር​ም​ያስ ሐሰ​ተ​ኛ​ውን ሐና​ን​ያን፥ “ሐና​ንያ ሆይ ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ላ​ከ​ህም፤ ነገር ግን ይህ ሕዝብ በሐ​ሰት እን​ዲ​ታ​መን አድ​ር​ገ​ሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ነቢዩም ኤርምያስ ነቢዩን ሐናንያን፦ ሐናንያ ሆይ፥ ስማ፥ ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል እንጂ እግዚአብሔር አልላከህም።

参见章节 复制




ኤርምያስ 28:15
20 交叉引用  

“ስለዚህ እነሆ እግዚአብሔር በእነዚህ ሁሉ ነቢያትህ አፍ የሐሰት መንፈስ አኖረ፤ እግዚአብሔርም ጥፋት እንደሚያመጣብህ ተናግሯል።”


ጳስኮር ሆይ፤ አንተና በቤትህ የሚኖሩት ሁሉ ወደ ባቢሎን ትጋዛላችሁ። አንተና በሐሰት ትንቢት የተነበይህላቸው ወዳጆችህ በዚያ ትሞታላችሁ፤ በዚያም ትቀበራላችሁ።’ ”


እኔ እነዚህን ነቢያት አልላክኋቸውም፤ እነርሱ ግን ለራሳቸው መልእክታቸውን ይዘው ሮጡ፣ ሳልናገራቸውም፣ ትንቢት ተናገሩ።


“አፈጮሌነታቸውን በመጠቀም፣ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል’ የሚሉትን ነቢያት እቃወማለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤


‘እኔ አልላክኋቸውም’ ይላል እግዚአብሔር ‘የሐሰት ትንቢት በስሜ ይናገራሉ፤ ስለዚህ እናንተንና ትንቢት የሚናገሩላችሁን ነቢያት አሳድዳለሁ፤ እናንተም ትጠፋላችሁ።’ ”


ሐናንያም በሕዝቡም ፊት፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ የናቡከደነፆርን ቀንበር ከሕዝቡ ሁሉ ጫንቃ ላይ ልክ እንደዚህ እሰብራለሁ’ ” አለ። በዚህ ጊዜ፣ ነቢዩ ኤርምያስ ትቶት መንገዱን ቀጠለ።


ከባልንጀሮቻቸው ሚስቶች ጋራ በማመንዘርና ያልነገርኋቸውን ቃል በስሜ በሐሰት በመናገር በእስራኤል ዘንድ በደል ፈጽመዋልና። ይህንም እኔ ዐውቃለሁ፤ ምስክር ነኝ” ይላል እግዚአብሔር።


የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በርግጥ እንዲህ ይላልና፤ “በመካከላችሁ ያሉት ነቢያትና ጠንቋዮች አያታልሏችሁ፤ የሚያልሙላችሁንም ሕልም አትስሙ፤


እናንተ ግን፣ ከንቱ በሆኑ የሐሰት ቃላት ታምናችኋል።


የነቢያቶችሽ ራእይ፣ ሐሰትና ከንቱ ነው፤ ምርኮኛነትሽን ለማስቀረት፣ ኀጢአትሽን አይገልጡም። የሚሰጡሽም የትንቢት ቃል፣ የሚያሳስትና ከመንገድ የሚያወጣ ነው።


እኔ ያላሳዘንሁትን ጻድቅ በውሸት ስላሳዘናችሁ፣ ኀጢአተኛም ከክፉ መንገዱ ተመልሶ ሕይወቱን እንዳያድን በኀጢአቱ ስላበረታታችሁት፣


ራእያቸው ሐሰት፣ ጥንቈላቸው ውሸት ነው፤ እግዚአብሔር ሳይልካቸው፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” ይላሉ፤ ይህም ሆኖ የተናገሩት ይፈጸማል ብለው ይጠብቃሉ።


እጄ የሐሰት ራእይ በሚያዩና በሚያሟርቱ ነቢያት ላይ ተነሥቷል። የሕዝቤ ጉባኤ ተካፋይ አይሆኑም፤ በእስራኤል ቤት መዝገብ አይጻፉም፤ ወደ እስራኤልም ምድር አይገቡም። በዚያ ጊዜ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።


ነቢያቷም በሐሰት ራእይና በውሸት ሟርት ይህን ሁሉ ድርጊት ያድበሰብሱላቸዋል፤ እግዚአብሔርም ሳይናገር፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል’ ይላሉ።


ማንም ትንቢት ቢናገር ወላጅ አባትና እናቱ፣ ‘በእግዚአብሔር ስም ሐሰት ተናግረሃልና ሞት ይገባሃል’ ይሉታል። ትንቢት ሲናገርም የገዛ ወላጆቹ ይወጉታል።


የእናትህ ልጅ ወንድምህ፣ ወንድ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወይም የምትወድዳት ሚስትህ ወይም የልብ ጓደኛህ፣ (አንተም ሆንህ አባቶችህ የማታውቋቸውን አማልክት) “ሄደን ሌሎችን አማልክት እናምልክ” ብሎ በስውር ሊያስትህ ቢሞክር፣


ነገር ግን እንዲናገር እኔ ያላዘዝሁትን ቃል በድፍረት በስሜ የሚናገርም ሆነ በሌሎች አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ ይገደል።”


跟着我们:

广告


广告