ኤርምያስ 25:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም27 “አንተም እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ጠጡ፤ ስከሩ፤ አስታውኩም፤ ዳግመኛም ላትነሡ በመካከላችሁ በምሰድደው ሰይፍ ፊት ውደቁ።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 አንተም፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በመካከላችሁ ከምልከው ሰይፍ የተነሣ ጠጡ፥ ስከሩም፥ አስታውኩም፥ ውደቁም፥ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሡም በላቸው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል አምላክ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ከማመጣው ጦርነት የተነሣ ሰክረው እስከሚያስመልሳቸውና ወድቀውም መነሣት እስኪሳናቸው ድረስ እንዲጠጡ የማዛቸው መሆኔን ለሕዝቡ ንገር፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 አንተም፥ “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመካከላችሁ ከምሰድደው ሰይፍ የተነሣ ጠጡ፤ ስከሩም፤ ተፍገምገሙ፤ ውደቁም፤ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሡም በላቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 አንተም፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመካከላችሁ ከምሰድደው ሰይፍ የተነሣ ጠጡ፥ ስከሩም፥ አስታውኩም ውደቁም፥ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሡም በላቸው። 参见章节 |