Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 25:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ስለዚህ ጽዋውን ከእግዚአብሔር እጅ ተቀብዬ እርሱ ወደ ላከኝ ሕዝቦች ሁሉ ሄድሁ፤ እንዲጠጡትም አደረግሁ፦

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ከጌታም እጅ ጽዋውን ወሰድሁ፥ ጌታም እኔን የላከባቸውን አሕዛብ ሁሉ አጠጣኋቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለዚህ ጽዋውን ከእግዚአብሔር እጅ ወሰድኩና እግዚአብሔር ወደ ላከኝ ሕዝቦች ሁሉ ሄጄ እንዲጠጡት አደረግሁ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ጽዋ​ውን ወሰ​ድሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እኔን የላ​ከ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛብ ሁሉ አጠ​ጣ​ኋ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ከእግዚአብሔርም እጅ ጽዋውን ወሰድሁ፥ እግዚአብሔርም እኔን የሰደደባቸውን አሕዛብ ሁሉ አጠጣኋቸው።

参见章节 复制




ኤርምያስ 25:17
9 交叉引用  

እንግዲህ፣ እንድትነቅልና እንድታፈርስ፣ እንድታጠፋና እንድትገለብጥ፣ እንድታንጽና እንድትተክል በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ዛሬ ሾምሁህ።”


ነገር ግን ጽዋውን ከእጅህ ለመውሰድና ለመጠጣት እንቢ ካሉ፣ እንዲህ በላቸው፤ “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በግድ ትጠጣላችሁ።


የሰሜንን ሕዝብ ሁሉ፣ አገልጋዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እጠራለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “በዚህች ምድርና በነዋሪዎቿም ላይ፣ በአካባቢዋም ባሉ ሕዝቦች ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ሰዎች የሚጸየፏቸውና የሚሣለቁባቸው፣ የዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ፤


ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሴዴቅያስ፣ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡት ሰዎች በኩል ለኤዶም፣ ለሞዓብ፣ ለአሞን፣ ለጢሮስና ለሲዶና ነገሥታት መልእክት ላክ።


“የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን ወደ ግብጽ ንጉሥ ወደ ፈርዖን አዙር፤ በርሱና በግብጽ ሁሉ ላይ ትንቢት ተናገር፤


ስለዚህ አፌን ከፈትሁ፤ እርሱም መጽሐፉን አጐረሠኝ።


ያየሁትም ራእይ ከተማዪቱን ለማጥፋት በመጣ ጊዜ ያየሁትን ራእይ የሚመስልና እንዲሁም በኮቦር ወንዝ ካየሁት ራእይ ጋራ የሚመሳሰል ነበር፤ እኔም በግንባሬ ተደፋሁ።


በክብር ፈንታ ዕፍረት ትሞላለህ፤ አሁን ደግሞ ተራው የአንተ ነውና ጠጣ፤ ኀፍረተ ሥጋህም ይገለጥ፤ በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ያለው ጽዋ ይመለስብሃል፤ ክብርህንም ውርደት ይሸፍነዋል።


跟着我们:

广告


广告