ኤርምያስ 24:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም3 እግዚአብሔርም፣ “ኤርምያስ ሆይ፤ የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም፣ “በለስን አያለሁ፤ ጥሩ የሆነው እጅግ መልካም ነው፤ የተበላሸው ግን እጅግ መጥፎ በመሆኑ ሊበላ የማይችል ነው” አልሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ጌታም፦ “ኤርምያስ ሆይ! የምታየው ምንድነው?” አለኝ። እኔም፦ “በለስን አያለሁ፤ እጅግ መልካም የሆነ መልካም በለስ፥ ከክፋቱም የተነሣ ሊበላ የማይችል እጅግ ክፉ የሆነ ክፉ በለስ ነው” አልሁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 እግዚአብሔርም “ኤርምያስ ሆይ! ይህ የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም “እነሆ የበለስ ፍሬዎችን አያለሁ፤ ጥሩዎቹ ፍሬዎች እጅግ የተዋቡ ናቸው፤ መጥፎዎቹ ፍሬዎች ደግሞ ለምግብነት ደስ የማይሉና እጅግ የተበላሹ ናቸው” ስል መለስኩለት። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 እግዚአብሔርም፥ “ኤርምያስ ሆይ! የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “በለስን አያለሁ፤ እጅግ መልካም የሆነ መልካም በለስ፥ ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ የሆነ ክፉ በለስ ነው” አልሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 እግዚአብሔርም፦ ኤርምያስ ሆይ፥ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦ በለስን አያለሁ፥ እጅግ መልካም የሆነ መልካም በለስ፥ ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ የሆነ ክፉ በለስ ነው አልሁ። 参见章节 |