ኤርምያስ 22:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፤ “ ‘ዋይ ወንድሜ! ዋይ፣ እኅቴን!’ ብለው አያለቅሱለትም። ‘ዋይ፣ ጌታዬን! ዋይ፣ ለግርማዊነቱ!’ ብለውም አያለቅሱለትም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ስለዚህ ጌታ ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፦ “ ‘ወንድሜ ሆይ! ወዮ! እህቴ ሆይ! ወዮ!’ እያሉ አያለቅሱለትም፥ ወይም፦ ‘ጌታ ሆይ! ወዮ! ግርማዊነቱ ሆይ! ወዮ!’ እያሉ አያለቅሱለትም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም የሚለው ይህ ነው፥ “እርሱ በሚሞትበት ጊዜ ‘ዋይ! ወዮ! ወንድሜ ሆይ!’ እያሉ በማልቀስ አያዝኑለትም፤ እንዲሁም ‘ጌታዬ ሆይ! ንጉሤ ሆይ! ወዮ!’ እያለ የሚያለቅስለት አይኖርም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፥ “ወንድሜ ሆይ፥ ወዮ! ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! እያለ የሚያለቅስለት ለሌለው ለዚያ ሰው ወዮለት! 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፦ ወንድሜ ሆይ፥ ወዮ! እያሉ አያለቅሱለትም፥ ወይም፦ ጌታ ሆይ፥ ወዮ! እያሉ አያለቅሱለትም። 参见章节 |