ኤርምያስ 13:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም27 በኰረብቶችና በሜዳዎች ላይ፣ አስጸያፊ ተግባርሽን፣ ምንዝርናሽንና ማሽካካትሽን፣ ኀፍረተ ቢስ ግልሙትናሽን አይቻለሁ። ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ወዮልሽ! ከርኩሰትሽ የማትጸጂው እስከ መቼ ነው?” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 አስጸያፊ ሥራሽን፥ ምንዝርናሽን፥ ማሽካካትሽን፥ የአመንዝራነትሽንም መዳራት በኮረብቶች ላይ፥ በሜዳም አይቻለሁ። ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ወዮልሽ! ለመንጻት እንቢ ብለሻል፤ ይህስ እስከ መቼ ነው?” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 እርሱ የሚጠላውን ነገር ስታደርጉ አይቶአችኋል፤ ከባልንጀራው ሚስት ጋር ለማመንዘር እንደሚጐመጅ ሰውና ባዝራ እንደሚፈልግ ሰንጋ ፈረስ፥ እናንተም የአሕዛብ አማልክትን ተከትላችሁ በየኰረብታው ራስና በየሜዳው ስትኳትኑ አይቶአችኋል። የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ፥ ወዮላችሁ፥ ከቶ ንጹሕ መሆን የምትችሉት መቼ ይሆን? 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 አስጸያፊ ሥራሽን፥ ምንዝርናሽን፥ ማሽካካትሽን፥ የዝሙትሽንም መዳራት በኮረብቶች ላይ፥ በሜዳም ላይ አይቻለሁ። ኢየሩሳሌም ሆይ! ወዮልሽ! ለመንጻት እንቢ ብለሻል፤ ይህስ እስከ መቼ ነው? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 አስጸያፊ ሥራሽን፥ ምንዝርናሽን፥ ማሽካካትሽን፥ የግልሙትናሽንም መዳራት በኮረብቶች ላይ በሜዳም አይቻለሁ። ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ወዮልሽ! ለመንጻት እንቢ ብለሻል፥ ይህስ እስከ መቼ ነው? 参见章节 |