ኤርምያስ 10:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም23 እግዚአብሔር ሆይ፤ የሰው ሕይወት በራሱ እጅ እንዳልሆነች፣ አካሄዱንም በራሱ አቃንቶ ሊመራ እንደማይችል ዐውቃለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 አቤቱ! የሰው መንገድ ከራሱ እንዳልሆነ አውቃለሁ፥ ሰውም አካሄዱን ለመምራት የሚራመድ አይደለም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 እግዚአብሔር ሆይ! ሰው በራሱ ሕይወት እንደማያዝበትና አካሄዱንም በራሱ ሥልጣን መቈጣጠር እንደማይችል ዐውቃለሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 አቤቱ! የሰው መንገድ ከራሱ እንደ አይደለ አውቃለሁ፤ ሰውም አይሄድባትም፤ መንገዱንም ጥርጊያ አላደረገም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 አቤቱ፥ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይደለ አውቃለሁ፥ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም። 参见章节 |