ኤርምያስ 10:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ስለ ስብራቴ ወዮልኝ፤ ቍስሌም የማይድን ነው፤ ግን ለራሴ እንዲህ አልሁት፤ “ይህ የኔው ሕመም ነው፤ ልሸከመውም ይገባኛል።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ስለ ስብራቴ ወዮልኝ! ቁስሌም የማይሽር ነው፥ እኔ ግን፦ “በእውነት የመከራ ቁስሌ ነው እርሱንም መሸከም ይገባኛል” አልሁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 የኢየሩሳሌም ሕዝብ እየጮሁ እንዲህ ይላሉ፥ “በብርቱ ስለ ቈሰልን ወዮልን! ቊስላችንም የማይፈወስ ነው፤ እኛ ግን ይህን ሁሉ መከራ መታገሥ የምንችል መስሎን ነበር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ስለ ስብራቴ ወዮልኝ! ቍስሌም ክፉ ነው፤ እኔ ግን፦ በእውነት የመከራ ቁስሌ ነው፤ እርሱንም መሸከም ይገባኛል አልሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ስለ ስብራቴ ወዮልኝ! ቍስሌም ክፉ ነው፥ እኔ ግን፦ በእውነት የመከራ ቍስሌ ነው እርሱንም መሸከም ይገባኛል አልሁ። 参见章节 |